ህወሓት መራሹ መንግስት በጭንቀትና በፍርሃት እየተናጠ መሆኑ ተሰማ

በመረጃ መረብ ሰንሰለቱ አማካኝነት ወደ መንግስት መዋቅር ዘልቆ በመግባት ያገኘው የታማኝ ምንጮች መረጃ እንዳረጋገጠው በሙስሊሙ ዑማ ላይ ከፍተኛ በደልና ጭቆና የፈፀመው ህወሓት መራሹ መንግስት በአሁኑ ሰዓት የሙስሊሙ ማህበረሰብ አጠቃላይ ሁኔታ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ዘፍቆታል ። በአሁኑ ሰዓት ሙስሊሙ ማህበረሰብ የትግል ስልቱን ቀይሮ ውስጥ ለውስጥ በመደራጀት አንድነቱን እያጠናከረ እና በተናጠልና በቡድን በመሆን ስለ ቀጣይ ትግሉ እየተወያየ ባለበት በዚህ ወቅት ህወሃቶች ” የሙስሊሙ ዝምታና ድምፁን ማጥፋት ” አሳሳቢ ነው በቀጣይ ምን ሊፈጥሩ እንደሚችሉ አይታወቅም በማለት ህወሃቶች በከፍተኛ ስብሰባ መጠመዳቸው ነው የታወቀው እንደ ምንጮቻችን ገለፃ መሰረት ህወሃቶች ባለፉት ቀናቶች በየክፍለ ከተማው ከሚገኙ ታማኝ ካድሬዎቻቸው ጋር ባደረጉት ዝግ እና ጥብቅ ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ የሙስሊሞችን ዝምታ አሳሳቢ ነው ስለዚህ ትኩረት ሰጥተን መከታተል አለብን ለዚህም ይረዳ ዘንድ ካድሬዎቻችንን ከመቼውም በበለጠ በመስጅዶች እና ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢ ማሰማራት አለብን በማለት ተወያይተዋል :: በሌላ በኩልም በየግዜው በድብቅ የሚያደርጉት ሚስጥራዊ ስብሰባ አፈትልኮ መውጣቱና በተደጋጋሚ በ BBN RADIO በኩል ወደ ህዝብ ጆሮ መድረሱ ከፍተኛ ራስ ምታትና የእርስ በርስ አመኔታ ማጣትን እንዳስከተለባቸው ለማወቅ ተችሏል :: የዚህን ዜና ዝርዝር በምሽቱ ፕሮግራማችን ይጠብቁን ፣

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.