ለቤይጂንጉ የዓለም ሻምፒዮና ከ7 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለሽልማትነት ተዘጋጅቷል

ብዛት ያላቸው ተወዳዳሪዎች የተካተቱበት ሶስተኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ዛሬ ማምሻውን ቤይጂንግ ደርሷል

በቻይና ዋና ከተማ ቤይጂንግ ከነገ ጀምሮ ለቀጣዮቹ ዘጠኝ ቀናት የዓለም ምርጥ አትሌቶችን በ47 ውድድሮች ለሚያፎካክረው 15ኛው የዓለም ሻምፒዮና የነጠላ እና የቡድን አሸናፊ አትሌቶች ሽልማት የሚሆን 7,194,000 የአሜሪካን ዶላር የቀረበ መሆኑ ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት በነጠላ ውድድሮች
ለወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዎች 60000 ዶላር
ለብር ሜዳልያ አሸናፊዎች 30000 ዶላር
ለነሐስ ሜዳልያ አሸናፊዎች 20000 ዶላር
ለአራተኛ ደረጃ 15000 ዶላር
ለአምስተኛ ደረጃ 10000 ዶላር
ለስድስተኛ ደረጃ 6000 ዶላር
ለሰባተኛ ደረጃ 5000 ዶላር
ለስምንተኛ ደረጃ 4000 ዶላር

በቡድን ውድድሮች
ለወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዎች 80000 ዶላር
ለብር ሜዳልያ አሸናፊዎች 40000 ዶላር
ለነሐስ ሜዳልያ አሸናፊዎች 20000 ዶላር
ለአራተኛ ደረጃ 16000 ዶላር
ለአምስተኛ ደረጃ 120000 ዶላር
ለስድስተኛ ደረጃ 8000 ዶላር
ለሰባተኛ ደረጃ 6000 ዶላር
ለስምንተኛ ደረጃ 4000 ዶላር የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የዓለም ሪኮርድ ለሚሰብሩ አትሌቶች የ100000 ዶላር ጉርሻ የሚሰጥ ሲሆን የጉርሻውን ሽልማት ወጪ የሚሸፍኑት የአይ.ኤ.ኤ.ኤፍ አጋር የሆኑት ቲዲኬ (የወንዶቹን) እና ቶዮታ (የሴቶቹን) ናቸው፡፡ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማሕበር የሪኮርዱን ሽልማት በተመለከተ ማግኘት የሚችሉት ሪኮርዱን የተስተካከሉ ሳይሆኑ የሰበሩ አትሌቶች ብቻ እንደሚሆኑ በግልፅ አሳስቦ የሽልማቱና የጉርሻው ክፍያ የሚፈፀመውም አትሌቶቹ የተለመደውን የአበረታች መድኃኒት ምርመራ ሂደት ካለፉ በኋላ እንደሚሆን አስታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.