ጥሮፈሰር ጌታቸው ኀይሌ በዝነኛው ንጉሠ ነገሥት ዘርዕ ያዕቆብ እና በታዋቂው ፈላስፋ ዘርዕ ያዕቆብ ላይ የብዕር ዘመቻቸውን አውጀዋል

በታሪኩ ውብነህ ጌታነህ

tarikuwgetaneh@gmail.com

በመጀመሪያ ማንነቴን ለመግለጽ እወዳለሁ፤ ታሪኩ ውብነህ ጌታነህ እባላለሁ። በዱቁና ሥራ በአንኮበር፤ ኪዳነ ምሕረት፤ በሰላ ድንጋይ ሥላሲ፤ በዶቃቂት ሚካአኤል፤ በማፉድ ሚኬኤል፤ በጉር ሥላሲ፤ በደብረ ሲና መዳሕኒዓለም፡ በደብረ በርሃን ሥላሲና በምጥማቅ አማኑኤል አገልግያለሁ። ዋዚማ ለጥቂት ግዚ ተጉለት በሚገኘው በአጃና ሚካኤል ተምሪአለሁ። አቋቋም ስለአልተማርኩ የመሪጊታነት ማዕረግ የለኝም። ክህነትም የለኝም። ይህም ሆኖ ካህናቱና ሊቃዉንቱ የሚሉት ይገባኛል። ሲሳቱም አውቃለሁ። ስህተቱም ቢገባኝም ማስተካከል አልችልም ። ሊቅ ሲሳት ማረም የሚችለው ሊላ ሊቅ ነው። ይህ ከጥንት ጀምሮ ያለ የተለምዶ ሕግ ነው። ጨዋ ካህናቱኑም ሆነ ሊቃዉኑቱን አያርምም፤ በተለምዶ ሕግ ጨዋ ዝም ነው የሚለው፤ ዝምም ስለሚል ማውቅ ያለማወቁ አይታወቅም፤ ስለዚህም ነው ጨዋ ተብሎ የሚጠራው። ከላይ በተጠቀሰው አርዕስት ላይ አስፈላጊውን ትችትና አስትያየት ለምስጠት ቡቁነቲ አጠራጣሪ ነው። እላይ እንደተባለው ጥያቀው የችሎታ ጉዳይ ነው። እኒ በሁለቱ ማህል ነኝ፤ በዱቁና ስለአገለገልኩ ከጨዋ በላይ ነኝ ፤ ተንስኡ ለጸሎት ብዮ ስለምጮህ። በሥርዕቱ ገፍቺ ስለአልተማርኩ ከካህናቱና ከሊቃወንቱ ወገንም አይደለሁም። እንዲት አድርጊ ነው እኝህን ታላቅ ምሁር በውውይት ገጥሚ የምተችው። እንዳአጋጣሚ ሆኖ ፕሮፈሰር ጌታችው ኅይሊ ምሁርነታቸው በዘመናዊ ትምህርት ስለሆንና ደገሞም የኒም ትምህርት በመጠኑ የዘመናችንን ትምህርት [ባይመጣጠንም] ስለሆነ ያየሁትን ስህተት ለመጠቆም እችላለሁ ብዮ እገምታለሁ፤ ከዚያም አልፎ በሚስጡት አስትያየት ላይ በትኩረት ተመልከቺ ለማረም ሳይሆን ክስተት የሆነዉን ለማመልከት በቂ የሆነ ችሎታ አለኝ ብዮ እገምታለሁ።

ፕሮፈሴር ጌታቸው ኅይሌ በረጅም ግዜ ታሪካቸው የሚታወቁት ውዳሴን አና ዝናን በመፈለግ ነው፤ በከፍተኛ ደረጃ የተማሩ መምሕር ሆነው ለምን ከንቱ የሆነውን ውዳሴ እና የማያስፍልገውን ዝና ፈለጉ ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፤ ይህ የኛ የኢትዮጵያውን ጎጄ የሆነ ባህላችን ነው፤ ፕሮፈሰሩ ወደው ሳይሆን ተገደው ነው፤ አንድ መምሕር በዕውቀቱ ብቻ ሳይሆን በተወሳሰበ መንገግድ ተከቦ ታጅቦና ሰሙ ገኖ መታወቅ አለበት፤ በረጅሙ ግዚ ታሪካችን ባህላችን የሚያንጸባርቅው በጉብዝናው የታውቀ ግለስብ በአምባገንነት አስፈራርቶና ረግጦ ሲገዛና ሲያስገዛ ነው፤ ይህ ከአልሆነ ብቁ መሪ አይባልም፤ በዝና የታወቀ ገናና መሪ ያስፈልጋል፤ አገራችን የጎበዝ አገር ነች፤ በቅርቡ አንድ ጎብዝ 20 ዓመት ደክመን የስራነውን ቢተክርስቲያን ከመተዳደሪያ ሕጋችን ውጭ በሆነ ኀይል ነጥቆ ሲወስድ አሱ ከሕግ በላይ መሆኑን አሳውቆ ነው፤ “አኛ ከሕግ በላይ ነን” ብሎ በአዳራሹ ሲንጎራደድ ካህናቱ በቅዳሲ፤ ደብተራው በዋዚማ፤ ዲያቆናቱና መዘምራኑ በጽናጽንና በከበሮ፤ ሲቱ በዕልልታ፤ ምዕመን በጭብጨባ ሲቀበለው የነበርው ስሚት የጋለ ነበር። ከጥቂቶች በስተቀር እሱን በሆንክ ያላለ ምዕምናን አልነበረም። በዚህ ማዕበል ዉስጥ ስለሕግና ሥርዓት መናገር ዘበት ነው፤ ውግዘቱና ቁጣው አይቻልም፤ ዓይንህ ለአፈር ይሁን ተብለህ ትገፈተራለህ፤ ከአቅም በላይ ነው። ቢተክርሲቲኒያችን በታሪኳ የምትታወቀው በክርስትናዋ ሳይሆን ለአምባ ገነኖች በምትስጠው አገልግሎቷ ነው። ይህ አዲስ ነገር አይደለም፤ ክርስትና ከተቀብልን ጀምሮ ያለ ነው። በረጅም ግዜ ታሪኳ ከፖሌቴካ ነፃ ሆና አታውቅም። የመንግስት ለውጥ በሚሆንበት ጌዜ ከሁሉ አስቀድሞ ቤተክርስቴኗን በመጀመሪያ መያዝ ግዲታ ነው፤ ተባባሬ የፖለቴካ አካል ስለሆነች። እያወደሰችና እየገዘተች ተገዥውን ታስተባብራለች። ገዥውን በጸሎት ጠላቱን በፍጥነት እንድያስገዛላት በቅዳሴ ግዚ ትማለዳለች፤ መብት መጠየቅ የናት እትዮጵያ ጠላት ነው፤ ይህ በምንባብ ግዜ ዲያቆኑ የሚለው ነው፤ ሥርዕተ ቅዳሴዉና ፖለቲካውን መለየት አይቻልም። ነገሩ የጎበዝ አገር የጎበዝ ቅዳሴ ሆኖ ነው እንጂ ሐዋሪያቱ እንደዚህ ብለው አልቀደሱም።   

 የጀግኖች ጀግና እንደተባለው መሪ መሆን የሁላችንም ፍላጎት ነው፤ አገራችን የጎበዝ አገር ነች፤ ጎበዝ ክሕግ በላይ ሆኖ የሚገዛት ነች፤ ይሕም ሆኖ ስለ አእገራችን ያለን አስተሳሰብ በጣም ከፍተኛ ነው፤ ከማንም የበለጥን ይመስለናል፤ የሚያስገርመው ደግሞ መብልጣችንን የሚያመለክት ምንም ነገር የለም፤ አሁን ይህ ሁሉ ስንክሳር አዚህ ለምን አስፈለገ? ቢባል የሐተታው አስፈላጊነቱ ፕሮፊሰር ጌታቸው ኅይሊ ምን በአጠፋሁ ነው እንደዚህ ዓይነት አቢቱታ የሚቀርብብኝ? ብለው ይጠይቁ ይሆናል፤ ስለዚህ መልሱ በቅድሚያ የተስጠ እንደሆነ በተረጋጋ መንፈስ መማማርና መተራረም የሚያስችል ሁናቲ ለመፍጠር ታስቦ ነው፤ በተጨማሪ ዉዳሲና ዝና ከላይ እንደተጠቀሰው ባሕላችን ስለሆነ ፕሮፈሰሩ ብቻቸውን አይደሉም፤ እኛ ከሳቸው እሳቸው ከኛ አንለይም፤ ልዩነቱ የሳቸው ፈር የለቀቀ እና ከቁጥጥር ዉጭ መሆኑ ብቻ ነው፤ ፕሮፈሰሩ በዚህ ጉዳይ ላይ የታውቁ ናቸው፤ ከሳቸው በላይ ሊላ አዋቂ ኤትዮጵያዊ የለም፤ ብቸኛውና ታዋቂው መምህር ፕሮፈስር ጌታቸው ኅይሊ መባል ግዲታ ነው፤ የአለምንም ጥርጥር ከላይ የተጠቀሰውን ጸሐፊ ፕረፈሰሩ “ደግሞ ‘ታሩኩ’ ብሎ ጸሐፊና ‘ታሪክ’ አዋቂ” ብለው እንደሚሉ በመረጃ ማቅርብ ይቻላል፤ የዚህም መረጃ ደግሞ ይህንን እንደሚሉ አትጠራጠሩ። ነገር ግን ይህንን ጎጂ ባሕል ተመልክተው ከተቀበሉት ታላቅ ምህሩነት ነው።

 እዜህ ልይ ግልጽ ለማድረግ የምፈልግው  በዚህ ጉዳይ ፕሮፈስሩ በስምምነትና በተረጋጋ መንፈስ አቢቱታዮን ኢንዲሰሙኝ ነው፤ በላይ በተሰጠው  አርዕስት ላይ የምሰጠውን አስትያየት ተመልክተው በተፈጠረው ያለመግባባት ላይ ሰፋ ያለ መግለጫ እንዲሰጡበት ነው።  ከዚህ ሊላ የታላቁን ምሁር ስም ዝቅ ለማድረግ ያለሞሆኑን መታወቅ አለበት፤  በተጨማሪ ከመጻፍ ይልቅ ማንበብን፤አስተያየት ከመስጠት በላይ መቀበልን፤ እጅግ በጣም አድርጌ ስለማምንበት አሳብ አፍላቄዎችና ጸሐፊዎችን ለማመስገን እወዳለሁ። ይህ የመጀመሪያ ጹሑፊ ስለሆነ ለማደርገው ስህተት አስቀድሚ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ነገር ግን እላይ በተስጠው አርዕስት መሰረት በሁለቱ ዘርዕ ያዕቆቦች [ይቅርታ ስም “አነ” ተብሎ መባዛት ነበረበት] ላይ ያቀረቡት ትንተና እና ውይይት በመረጃ ተደግፎ የአነዚሀን ሁለት ታላቅ ኤትዮጵያውያንን ታሪካዊ ሄደትን የሚያንጸባርቅ ከሆነና  ይህ ጽሑፍ  ደግሞ የፕሮፈሰሩን ሥራ ለማሰነስ በመረጃ ከተረጋገጠ ፕሮፊሰሩን ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁ መሆኒን እንዲታውቅልኝ እፈልጋለሁ፤ ነገር ግን የፕሮፈሰሩ ትንተና እና የስጡት አስተያየት መሰረተቢስ ከሆነና ከዚህ በፊት የሰሩት ሥራዎች እንደሚመሰክሩት ውዳሲንና ዝናን ለማትረፍ ከሆነ ፕሮፊስር ጌታቸው ኅይሌ በጽሑፍ የሚይስፈልገውን እርማት ማድረግ ታሪካዊ ግዲታቸው ነው ብዮ አምናለህ። እውነት አንድ ነው፤ ስለሆነም ያለምንም ፍርሐት መነገር አለበት፤ እውነት ዋነኛ የችግር መፍትሄ ነው። እዚህ ላይ ለፕሮፊስሩ መንገር የምፈልገው ተማሪ ሆኚ የተማርኩትና ምንም ጊዚም የማይረስኝን ትምሕርት የጊታዉና የባሪያው ታሪክ ነው፤ ባሪያው ለጊታው በየግዚው ሰዉነቱ እንድማንኛውም ሰው ነው፤ እነደሰው ሁሉ ያስባል፤ ይርበዋል፤ይጠማዋል፤ ይደክመዋል እነደሰው ሁሉ እረፍት ያስፈልገዋል፤ እንኳን ሰው ቀርቶ እንስሳትም የሰው ልጅ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ እነሱም ይፈልጋሉ እያለ ለጊታው ያጫውተው ነበር። ኬዕለታት አንድ ቀን ጊታው የባሪያው አቢቱታ ህሊናዉን ስለአስጨነቀው በነፃ አሰናበተው። እርስዎ ታላቅ ምሁርና ጊታ ነዎት፤ እኒ ደግሞ የአሽክር ልጅ ነኝ፤ በቢቲሰቢ ምህላ አለ፤ ከትውልድ ትውልድ ለአገራችን በአሽክርነት እንድናገለግል ቋሚ ትዕዛዝ ነው፤ነገር ግን ለግለሰብ አገልጋይ ሆነን አገርን ክጎዳን ዕርግማኑ ከፍ ያለ ነው። እርሶዎም የአሽከሩን ልጅ አቢቱታ በጥሞና በሕሌናዎ እንዲመለከቱት በአክብሮት እጠይቃለሁ። መልካም ንባብ።

 

አንደኛ፡ ስለፈላስፋው ዘርዕ ያዕቆብ የተሰጠው ትርጉምና አና ትንተና

“ሐተታ ዘዘርአ ያዕቆብ በሚባል ሰም የሚታወቀው የወርቂ የሕይወት ታሪክ”

ትርጉም  በጊታቸው ኅይሌ

ኮሌጅቬል [ሚኒሶታ] 2006

ፕሮፊስር ጊታቸው ትንተናቸውን የሚጀምሩት በመዘከር ነው፤ሐተታ ዘዘርአ ያዕቆብን ከግዕዝ ወደ አማርኛ እንድትተረጉመው የገፋፋኘ አቶ አሰፋ ገብረ ማርያም ስለሆነ መታስቢያው ይሁንልኝ፤ብለው ወደራሳቸው ትንተናመቅድምይገባሉ፤ ይህ ከትርጉሙ በፊት በመጀመሪያው 12 ገጾች የተጻፈው አስተያየት ነው፤ ከአስተያየቱ መጨረሻ ገጽ ላይ እንደተጻፈው ተጽፎ የተጠናቀቀው የካቲት 15 ቀን 2006 ነው [February 22, 2014] አስራምስት ክፍል ያለው በግዕዝ የተጻፈው ሐተታ 32 ገጽ የያዘ ትርጉም ነው፤ እንደሚመስለኝ መጽሐፉ ሙሉ በሙሉ የተተረግጎመ አይመስለኝም፤ ሆኖም ፕሮፊሰር ጊታቸው ኅይሌ ሙያቸው ትርጉም ስለሆነ ሥራው በሚገባ ተስርታል ማለት ይቻላል፤ ችግሩ ግን አስተያየቱና ትርጉሙ ፈጽሞ አይገናኙም፤ እዚህ ላይ የሚሰጠው ትችት ፕሮፊሰሩ በዘርዕ ያዕቆብ ፍልስፍና ላይ በስጡት አስተያየት ብቻ ይሆናል፤ አንባቢም ተሳትፎ አስትያየት እንዲስጥበት አስተያየታቸውን በአባሪነት ይቀርባሉ፤ እዚህ ላይ አንባቢ እንዲገነዘበው የማሳስበው ፕሮፊሰሩ  የተጠቀሙትአልፍ” “ሲሆን እኒ ደግሞ  “ዐይን” “ነው፤ ፕሮፊስር ጊታቸው ኅይሌ የቋንቋ መምሕር ሰለሆኑ ምናልባትአልፍ”  “ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እኔ ፊደል በቆጠርኩበት አካባቢ ዘርዕ ያዕቆብ የሚጻፈውበዕይን” “ነው፤ ይህ ለትችት ሳይሆን አንባቢ እንዳይደናገር በማለትና አይነተኛ የአጻጻፍ ስልት ሊኖረን ይገባል ብሎ ለማሳሳብ ነው፤ በተልይ የቋንቋ መምሕር ግድየለሽ ሊሆን አይገባም።  

ፕሮፈሰር ጊታቸው ትንተናቸውን የሚጀምሩት ታዋቂ ናቸው ብለው በሚያስቧቸው አውሮፓውያን ሊቃውንት ነው። ወዳጃቸው አቶ አስፋ ገበረ ማርያም ፕሮፈሰሩን የጠየቁትና የገፋፉት በግዕዝ ዘርዕ ያቆብ የጻፈውን ፍልስፍና ወደ አማርኛ እንዲተረጉሙትና እኛ ኢትዮጵያውያኖች የራሳችን ፈላስፋ የሚለዉን አንብበን እንድንረዳ ነበር። አቶ አስፋ ገብረ ማርያም ከዚህ ውጭ ሊላ ነገር የሚፈልጉ አይመስልም። የጠየቁት እንዲተረጎምላቸው ነው። ለዚህም ነውመታሰቢያው ይሁንልኝያሉት። ቃል በገቡት መሰረት በቀጥታሐተታ ዘዘርአ ያዕቆብን ከግዕዝ ወደአማርኛተርጉመው ለወዳጃቸው መታሰቤያ ቢያበረክቱ ኖሮ እዚህ ውይይት ከመግባት ይልቅ አማርኛውን እያነበብን ፍልስፍና ምን እንደሆነ እንማረበት ነበር። ነገር ግን ከዘርዕ ያቆዕብ ፍልስፍነ አስቅድመው የራሳቸውን ትንታኔ በአውሮፓውያን ሊቃውንት አጅበው አቀረቡ። እዚህ ላይ አንባቤ በትኩረት መምልከት ያለበት ፕርፈሰሩ በቅድሚያ አሳባቸውን መስጠት የለባቸውም ማለት አይደለም፤ በአግባቡ ሊሰጡ ይችላሉ፤ አግባብ ማለት ሥርዓት ማለት ነው። 12 ገጾች ላይ የተጻፈው መቅድም ከሥርዓት ውጭ ነው። ፕሮፊሰሩ ራሳቸውን ከማንኛውም ሥርዓት በላይ [ከሕግ በላይ ነኝ እንዳለው ጎበዝ ማለት ነው] ነኝ ስለሚሉ ይህንን አስትያየት አይቀብሉም፤ እሳቸው ተቀበሉት አልተቀበሉት ምንም የሚያመጣው ለውጥ የለም። ነገር ግን ለአንባቢ ሥርዓት አልባ መሆን ሕብረተስብን አጥፊ መሆኑን ለመጦቆም ነው። አገራችን የጠፋችው ከሕግ በላይ ነን በሚሉ አምባገነኖች ነው፤ ፕሮፊሰሩ ሞገደኛ አምባ ገነን መሆናቸዉን አያውቁትም፤ ይህ የአምባ ገነኖች ባሕርይ ነው። በሥነ ጹሕፍ ደንብ  ሥርዓቱ እንዲት እንደተጣሰ በዝርዝር አስረዳለህ። 

 

አንደኛ፡ በመጽሐፉ አርዕስት መሰረት ስምም ጸሐፊም አሉት፤ ጸሐፊው የመጻሐፉ ባለቢት ነው፤ አርዕስቱ ፍልስፍና ነው። እንግዲህ ዘርዕ ያዕቆብ ባለቢት ሲሆንሐተታየተባለው ደግሞ አርዕስት ይሆናል ማለት ነው። በሥነ ጽሑፍ ሥርዕት መሰረት ባለቢት በተቀዳሚነት ይቀርባል፤ አቀራረቡ ቅደም ተከተሉን ከተከተለ ትንታኒውን አቅራቢ በመሰለው መንገድ ስለባልቢቱ ሊያቀርብ ይችላል፤  በመጀመሪያ ደርጃ ባለቢቱን ማስተዋወቅ አለበት፤ ትምህርቱን ሙያዉን ሥራውን አጠር በአለ መልኩ ለአንባቢ ማስተዋወቅ ግዲታ ነው፤ ከዚህ በመቀጠል በተሰጠው አርዕስት ላይ ለመጻፍ ምን እንዳነሳሳው አጠር ያለ መግለጫ መስጠት አስፈላጊ ነው። ለዚህም መረጃ የሚሆን ከመጻሕፉ ላይ ቀንጠብ አድርጎ ማቅረብ ለሚሰጠው ትንተና ግልጽና ተጨባጭ የሆነ መረጃ ይሆናል፤ ለምሳሊ መጽሐፉን ለመጻፍ ምን እንዳስገደደው መጥቀስ አስፈላጊ ነው።

 

ሁለተኛ፡  ስለአርዕስቱ ሰፋ ያለ መግለጫ መስጠት ግዲታ ነው፤ አንባቢው ትምህርት ማግኝት የሚችለው አርዕስቱ ምን እንደሆነ ሲገባው ነው፤ ይህ ከአልሆነ ለማንበብ ፍላጎት አይኖረውም፤ ስለዚህ ፍልስፍና ምን እንደሆነ ቃል በቃልም ሆነ በምሳሊ ማስረዳት እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፤ ለምሳሊ ፍልስፍና ማለት የሥነ ፍጥረትን ሁኒታ በአንክሮ መመልከት ነው ማለት ይቻላል፤ ግን ይህ በቂ ሊሆን አይችልም፤ የፍልስፍና ታሪካዊ ሄደት በሚገባ መቅረብ አለብት።

 

ሶወስተኛ፡ በዚህ ጽሑፍ ላይ የቀረበ አስተያየት ወይም ትችት ከአለ በአጭሩ ከመረጃ ጋር ማቅረብ ለአንባቢው የበለጠ ትምህርት ይሰጣል፤ የራሱኑም አስተያየት እንዲሰጥ ይገፋፋዋል፤ በተጨማሪ ሃሳብ በነ ፃነት ሲንሽራሸር መላምቱ ይዳብራል፤ ውጢቱም የተሳካ ይሆናል። በፍልስፍና ላይ የሚደረግ ውይይት ማለቂያ የለውም፤በየምክናያቱ ሁኒታዎች ይለዋወጣሉ፤ ፍልስፍናሁኒታን” ለዋጭ ኅይሎችን በትኩረት ይመለከታል፤የወጣ ይወርዳል፤ የወረደ ደግሞ ተመልሶ ይወጣል፤ ይህ ፉጡራዊ ሕግ ነው፤ የዚህን ፉጡራዊ ሕግ ፈላስፋ ይመረምራል፤ የመመርመሪያውም የራሱ የሆነ ልዩ ዘዲ አለው፤ እንግዲህ ከላይ የተጠቀሱተን የሥነ ጽሑፍ መምርያ መሰረት በአጭሩ ስለ ፈላስፋው ዘርዕ ያቆብ በቅደም ተከተል ይቀርባሉ። ይህ መሰረታዊ የሆነ የሥነ ጽሑፍ ታሪካዊ ሄደት ነው፤ ይህም ሆኖ ለተለያዩ ትምህርት የየራሱ ዘይቤ አባባልና ቋንቋ ቃላት አገባብና ዕረፍተ ነገር አሰካክ አለው፤ የግስ እርባታዎች፤ መስተዋድድና መስተፃምር፤ ገቢርና ተግብሮ፤ በሳቢና ቤተሳቢ ዘርፍ በትክክል ሕጋቸውን ማንፀባረቅ አለባቸው። በፍልስፍና ላይ ዝርክርክ የሆነ ዕረፍተ ነገርና ደረጃውን ያልጠበቀ ቃላት አይጻፍም። የአጻጻፉን ምሳሊ እንመለከት።

 

ዘርዕ ያዕቆብ የብዕር ስሙ ነው። እርሱ ግን የክርስትና ስሜ ነው በሎ ጽፏል፤ ደግሞ የመጠሪያ ስሜ ወርቄ ነው ይላል፤ ነገር ግን ፍልስፍናዉን የጻፈው መጽሐፍሐተታ ዘዘርዕ ያዕቆብበሚል አርዕስት ነው። የትውልድ አገሩም አክሱም ነው ይላል፤ አክሱምም በሚኖርበትም ግዚ የሚታወቀው በወርቄ ነው ይላል። እዚህ ላይ አንባቢ በቱከረት መመልከት ያለበት የዚህ ፍልስፍና መጽሐፍ ጸሐፊ በውነተኛ ስሙ መጠራት ያለመፈለጉን ነው። ለምንድነው በስሙ መታወቅ ያልፈለገው? ይህ ይህንን መጽሐፍ እንመረምራልን የሚሉ ጸሐፊዎች ስራ ነው። ይህ ከተባለ በኋላ ምክናያቱን መፈለግ ነው። በመጽሐፉ ላይ የተጻፈው ስለሚያስጠየቅዉና ስለሚያስከስሰው በብዕር ስም ተደብቆ ስለመጽፉ ምንም ጥርጣሪ የለም፤ የትም አገር ተሂዶ ቢፈለግ ወርቄ የሚባል ሰው አይገኝም፤ ይህ መላ ምት ነው፤ ማለትም ሊሆን ይችላል ተብሎ ነው፤ላይሆንም ይችላል፤ ነገርግን በዚህ ላይ ሃሳብ ቢንሸራሸር ከዚህ የተሻለ መላ ምት ሊመጣ ይችላል። እዚህ ላይ በፍልስፍና ሙያ የተሰማሩ ሊቃውንት በአንድነት የሚስማሙት ነገር ቢኖር ዘርዕ ያዕቆብ በብዕር ስም ተደብቆ የጻፈበት በቂ የሆነ ምክንያት አለ፡ እሱምሁኒታ” ይባላል። ዓለማዊና መንፈሳዊ በመጽሐፍ ላይ በአንድነት ሆነው ተተንትነው ሊጻፉሁኒታው” አይፈቅድም። መጽሐፉ እንደተግኝ ሃይማኖተ ቢስ ተብሎ ተውግዟል፤ ጸሐፊውም ቢገኝ ኖሮ በመቋሚያ ተደብድቦ ይገደል ነበር። ይህ ስለ ዘርዕ ያዕቆብ ማንነት የተስጠ አጭር መግለጫ ነው። ስለትምህርቱና ሙያው አርስቱ ላይ በሚደረገው ውይይት በአጭሩ ይጠቀሳል።

 

ስለ አርዕስቱ ሰፋ ያለ መግለጫ መስጠት አስፈላጊ ነበር፤ ነገር ግን ይህ በአጭሩ የተጻፈ አስተያየት ስለሆነ በዝርዝር ስለፍልስፍና ታሪካዊ ሄደት ማቅረብ አስቸጋሪ ነው፤ ስራው ብዙ ነው፤ ከላይ እነደተጠቀሰው ፍልስፍና ማለት የሥነ ፍጥረትንና የሕብረተሰቡን ሁኒታ መመርመር ማለት ነው፤ እጅግ በጣም ሰፊ ስለሆነ ፍጡራዊና ሰው ሽራሽ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ትኩረት በተሞላበት ዘዲ ይመረምራል፤ ተመራምሮ ዉጢቱን ለሕብረተሰቡ ያሳውቃል፤ ያስተምራል፤ የወደፊቱንሁኒታ” በትንቢት ሳይሆን በምርምር ጠንቅቆ ያውቃል፤ሁኒታዎችእንዲት እንደሚከሰቱና እንዲት መለወጥ እንደሚችሉ ጠንቅቆ ያውቃል። ዘርዕ ያዕቆብ ጹሑፉ ላይ እንደሚታየው በታላቅ ደረጃ የተማረ ሊቅ ነው፤ ዳዊት አንብቧል፤ ሕገ ኦሪትንና ሕገ ወንጊልን  በሚገባ ያውቃል፤ ሙያው ማሰተማር መሆኑን አያጠራጥርም፤ ጽሑፉኑም የጻፈው በሚያስተምርበት ወቅት ነው፤ ዋሻ የተባለው እንደስሙ መደቢቂያ እንጂ የጽሑፉ መጻፊያ ስፍራ አልነበረም፤ የኢትዮጵያ ታላላቅ መጻሕፍት የተጽፉት በገዳም ውስጥ ነው እንጂ በዋሻ አይደለም፤ ብራናው ተፍቆ ብዕሩ ተቀሮዖ ቀለሙ ከተለያዩ ንጥረ ነገሮች ተበጥብጠው የሚሰሩት በትምህርት ቢት አካባቢ ነው፤ ዋሻ ውስጥ ተደብቆ እነዚህን ሁሉ አቀነባብሮ በሁለት ዓመት ውስጥ የፍልስፍና መጽሐፍ ጻፈ ማለት ያስቸግራል፤ በአጭሩ ፍልስፍና ዋሻ ውስጥ ተደብቆ በጾም በፅሎት የሚመጣ ነገር አይደለም፤ ከሕብረተስቡ ጋር ሆኖሁኒታዉንበትኩረት ማጥናት ግዲታ ነው። ዘርዕ ያዕቆብ ምናልባት ትውልደ ቢተ እስራኢል ሳይህን አይቀርም የማለት ግምት አለኝ፤ በውይይቱ ላይ ሃይማኖትን አጥብቆ የዚህ ወገን ወይም የዚያን ወገን አይልም፤ እምነት አንድ ነው አንዱ ከሊላው አይበልጥም ይላል፤ ፈጣሪዉንም ይጠይቃል፤ ለምንደነው ላንዱ ተገልጦ ለሊላው የማይገለጠው ብሎ ከራሱ ጋር ይወያያል፤ ችግሮች የሚፈቱት በውይይት ነው፤ፍልስፍና ማለት ይህ ነው። ሐተታዎቹ ብዙ ስለሆኑ አንባቢ ግዜ ወስዶ ሙሉ መጽሐፉን ማንበብ ይኖርበታል። ሐተታ ስለተባለው በመጽሐፉ ላይ ከተሰጡት አስተያየቶች ጋር በአጭሩ እንወያያለን።

 

በሶወስትኛ ደረጃ ስለሐተታ ዘዘርአ ያዕቅብበሚሰጠው አስተያየት ላይ ስለ መጻሐፉ ቀደም ብሎ የተሰጠ ትችት ከአለ እንደአስፈላጊነቱ በአባሪ ማቅረብ አስፈላጊ ነው። ይህም ሲባል ጸሐፊ መጽሐፉን ስለተቸ ብቻ በውዋቢነት መቅረብ የለበትም ትችቱ በበቂ መረጃ ታግዞና ደረጃውን ጠብቆ የተጻፈ ጽሑፍ መሆን አለብት። ነገር ግን በቅድሚያሐተታስለተባላው በቅጡ መዋያየት አስፈላጊ ነው። ቡዙዎቻችን ስለ ዘርዕ ያዕቅብ የሰማነው ክላውድ ሳምነር የሚባሉ በአዲስ አበባ ዩነቨርስቲ የፍልስፍና ፕሮፊሰር በአሳታሙት መጽሐፍት ላይ ነው፤ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ፍልስፍና በሚለው መጽሐፋቸው ውስጥ የዘርዕ ያዕቆብና የወልደ ሕይወት Treatise በሚል አርዕስት 1994 [. .]የታተመ መጽሕፍ ነው፤ ፕሮፊሰሩ በእንግሊዘኛ የተጻፈውን “treatise” የሚለውንሐተታብለው ተርጉመዉታል፤ መምሕሩ ከአምሳ ዓመት በላይ በዩነቨርስቲው ስለቆዩ ምናልባትሐተታያሉት ትርጉም በፍልስፍና ዓለም ውስጥ ትክክለኛ ሊሆን ይችላል፤ ወይም ደግሞ በጉባኤ  “ሐተታማለት የፍልስፍናን ውውይት ውጢት ያንጸባርቃል ተብሎ ተደንግጎ ሊሆንም ይችላል፤ነግር ግን በእርግጠኛነት ሆኚ እዚህ የሐተታን ትርጉም ልጽፍ አልችልም፤ ግን ከአንባቢ ጋር መወያየት የሚያስፈልገውሐተታየተባለው ቃል አመጣጡንና ይዘቱን ነው፤ አመጣጡ ሐተተ ከሚለው ግሥ ነው፤ ይዘቱ ደግሞ በተለምዶ አማርኛሐተተማለት ነገር አበዛ ይሆንናሐተታትህን አታብዛይባላል፤ ይህም ማለት አጠር አድርገህ አስረዳ ማለት ስለሆነ “Treatise” ለተባለው ቃል ትክክለኛ  መግለጫ ሊሆን  አይችልም፤ ሆኖም ሊቃውንቱ ተወያይተው በስምምነት ይሁን ከተባለ ሕግ ስለሆነ መከበር አለበት። በዚህ ሙያ የተስማሩ መምሕራን በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ድረስ የሰጡት መግለጫ ስለሊለ ሃሳብ እንዲሽራሽርበት ለየት በአለ ቃል ይቀርባል። ለግዚው “Treatise” የተባለውን ቃልንጥረ ነገርብለን መተርጎም ግዲታ ይሆናል፤ ይህም ማለት ሃሳቦች በውይይት ተንሽራሽረው በመጨረሻ በስምምነት የተገኘ ነገር ማለት ነው፤ ሆኖም እንደዚህ አይነት አገላለጽ በአንድ ግልስብ የሚወሰን አይድለም፤ መወሰን ያለበት በጉባኤ መሆን አለበት፤ ጉባኤ ደግሞ የሚሰየየመው በሊቃውንቱ ነው፤ ባሁኑ ግዚ ኢትዮጵያ እንኳንስ ሊቃውንት ቀርቶ የሊቃውንት ደቀ መዛሙርት የላትም፤ ከፍ ያለ የአገር ውድቀት ነው፤ ሊቃውንት የሚያስገኝሁኒታእስኪፈጠር ድረስንጥረ ነገርየተባለውን ለግዚው ተቀብሎ መወያየቱ አይከፋም። ከእንግዲህ ወዲህ ውይይቱ የሚቀጥለውንጥረ ነገርእየተባለ ይሆናል።

 

ይህንን ግዚያውዊንጥረ ነገርተብሎ የተተረጎመውን ቃል ትርጉሙን ማስረዳት አስፈላጊ ነው። ቀጥተኛ ትርጉሙ እንዲህ ሊሆን ይችላል፤ ፈላስፋው አንድ ነገርን መርምሮ አንጥሮ አጥሎና አስተካክሎ በጽሑፍ ሲያቀርብና ሊሎች ፈላስፋዎች ይህንን ግኝት አጥንተውና መርምረው ዕውነት ነው ብለው ምስክርነታቸውን ሲሰጡ ግኝቱ በእርግጥ ራሱን የቻለ ፍልፍስፍና ይሆናል። ይህም ሆኖ ፈላስፋ ሁሉ በንጥረ ነገር የተደገፈ አዲስ ነገር ይፈልስፋል ማለት አይደለም፤ በዓለም ሁሉ ከአሉት ፈላስፋዎች በንጥረ ነገር የተደገፈ ፍልስፍና ያገኙ በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። ፈላስፋዎች ሁሉ ያለሟቋረጥ ይመራመራሉ፤ ሥነ ፍጥረተን የማይመራመር ፈላስፋ አይባልም፤ ዘርዕ ያዕቆብ ሥነ ፍጥረትን የተመራመረ ፈላስፋ ነው። ነገር ግን ፕሮፊሰር ሳምነር እንደሚሉት ንጥረ ነገር የተደገፈ ምንም ዓይነት አዲስ ግኝት የለውም፤ ውይይቱ ሁሉ አለማዊና መንፈሳዊ ሆኖ በውስጣቸው ያለውን ቅራኒ ለመቅረፍ በሚገባ ተወያይቷል፤ ለፈጣሪው አግባብ ያላቸውን ጥያቂ አቅርቧል፤ የተለያዩ እምነት ተከታዮችን ተችቷል፤ ስለንብ ሥራ ሲፈላሰፍ እንዲህ ይላል፤ንቢቱ የተለያዩ አበባዎችን ትቀስማለች፤ በዚህም ምክናያት ጣዕም የሚሰጥ መዓዛው የሚጣፍጥ ማር ትሰራለች፤ ማርም ለሰው ልጅ እርካታ የሚሰጥ መጠጥ ይሆናል፤ በተጨማሪ ለጨለማው በርሃን የሚሰጥ ጧፍም ይሆናል፤ የሰውም ልጅም አንድንቧ ከተለያዩ ሁኒታዎች ቢቀስም ዕውቀትን ያገኝ ነበር ይላል [ከላይ የተጠቀሰው ከመጻሕፉ ላይ ሳይሆን በአእምሮዮ ያስታወስኩትን ነው] ስለ ሥነ ፍጥረት ሲፈላሰፍ ደግሞፍጥረት ያለ ፈጣሪ ሊኖር አይችልምይላል።

 

 በተጨማሪ ፈላስፋው በክፍል አንድ ላይ ስለትውልደ አገሩ በአጭሩ አስረድቶአል፤ ነገር ግን ከአጻጻፉ ላይ አንባቢ በአትኩረት መመልከት ያለበትየቅዱሳተ መሳሕፍትን ትርጓሜ ለመማርከአገሪ ርቄ በመሄድ በአገራችንና በውጭ መምሕራንትርጓሚን ተማርኩየሚለዉን መነሻ ነው፤ መድረሻው ደግሞ የሁለቱንም የመጽሕፍ ትርጓሚ ሕሊናዮ አልቀበል ስለአለዝም አልኩያለውን ነው፤  በዚህ መነሻና መድረሻ ረገድ ዘርዕ ያዕቆብ ከሁለቱም የተለየ ነፃ የሆነ ሕሊናውነት አዳብሮ መመራመር ጀመረ ማለት ነው። ዝም ያለበትም ምክናያት በነፃነት ማሰብ የማይቻልበት ሁኒታ ስለሆነ ነው፤ ለዚህም ከጽሑፉ በላይ የሚቀርብ መረጃ አይኖርም።  በክፍል ሁለት ላይ ዘርዕ ያዕቆብ የሚያሳየን በግዚው የነበረውን ክፋትና ጭካኒ፤ ሰው በሰው ልጅ ላይ የሚያደርገውን በደል ነው፤ ለዚህም መረጃ የሚሆነው የሚኖርበትን ዋሻ እንደመንግስተ ሰማያት አድርጎ መምለከቱ ነው፤ ይህም የሚያሳየው ሰው ምን ያህል ክፉ እንደሆነ ነው። እዚህ ላይ ተመራማሪ ፈላስፋ በትኩረት ማየት ያለበት በዘርዕ ያቆብ ግዜ የነበረውን ሁኒታንና የአሁኑን ነው። እንግዲህ የዘርዕ ያዕቅብን ፍልስፍና የምናየው ከሥነ ጹሑፍ ሄደትና ክሕብረተሰቡ ታሪካዌ ሄደት ጋር ይሆናል። ፍልስፍና ሕብረተሰብና ሥነ ጹሑፍ አንድ ናቸው፤ ለነዚህ አንድነት ሁኒታ ከአልተፈጠረ ሕበረተሰቡ ታሪካዊ ሄደት አይኖረውም። እንደዚሁ መንሰዋለል ይሆናል፤ ፍልስፍናም ታሪክም ሥነ ጽሑፉም አይኖረዉም፤ እረኛው እንደጠፋበት በግ ይበታተናል፤ አቅጣጫዉንም የሚሆነውንና የማይሆነዉን ለይቶ ሊያውቅ አይችልም፤ ወደተፈለገበት የሚነዳ የሚዳአሕያሆኖ ይቀራል።ይህም ስለሆነ ግብዞችና የበላይ ነን የሚሉ አካል አሸከሮች ለሰው ልጅ የሚሰጠዉን ክብር ነሰትውአሕያእንደሚሉት ነው።ዘርዕ ያቆብ በሥነ ጽሑፉ ላይ ትቶሉን ያለፈው ፍልስፍና የሚያሳየው በግዜው የነበረዉንሁኒታ” ነው። በጽሑፉም እያንዳንዱ ቃል የሚያንጸባርቁት ሕብረተሰቡን ያለብትን ሁኔታና ሕሊናዊነት ነው፤ ይህም ማለት በተወሰነ ስፍራና ግዜ ሁኒታው አስገድዶ የሕበረተሰቡ ሕሊናዊነት በጽሑፍ ሰፍሯል ማለት ነው፤ ጽሑፉም የሚያመለክተው በላይ በተጠቀሱት መላምቶች ተቀነባብሮ በአጋጣሚ ሳይሆን በታሪካዊ ሄደት የተገኘ ዉጢት ነው፤ የዘርዕ ያዕቅብም ፍልስፍና ዉጢት በታቀደው መሰረት የሰው ልጅ ለሚያደርገው ተግባር ሁሉ ሥርዓት እንዲኖረውና የተፈጥሮ ሕግን እንዲከተል ነበር።

 

 ነገር ግን ፈላስፋው በጽሑፉ ላይ እንዳለው በዘመኑ በተረጋጋ መንፈስ ፍጥረትን መመራመር ስለማይቻል በብዕር ስም ተደብቆ የፉጡራዊ ታሪካዊ ሄደትን ለማካፈል ጥረት አድርጓል። እንጊዲህ አንባቢ በትኩረት መመልከት ያለበት በዘመኑ የነበሩት ሊቃውንት የዘርዕ ያዕቆብን ሥነጹሑፍ ተመልክተው ቢወያዩበት ኖሮ የሕብረተሰቡ ታሪካዊ ሄደት የት ይደርስ ነበር? ብሎ መመራመሩ አግባብ ነው ብዮ አስባለሁ። ነገር ግን የዘርዕ ያዕቆብ ሥነ ጽሑፍ እንደ ሃይማኖተ ቢስ ስለተቆጠረ ተወገዘ፤ የሥነ ጽሑፍም ታሪካዊ ሄደት በአለበት ቆመ፤ ለዚህም መረጃ የሚሆነው የሕብረተሰባችን ያለብተን ሁኒታ ነው፤ ሥነ ጽሑፍ አልባ መሆን እርግማን ነው፤ በአለፈው አንድ መቶ ዓመት ውስጥ ሥነ ጽሑፍ ተብሎ ሊጠቀሱ የሚችሉ ከሶወስት ወይም አራት አይብልጡም፤ ሕሩይ ወልደሥላሴ [የሥነ ጽሑፍ ሊቅ] ከበደ ሚካኢል [የስንኝ ሊቅ] ሐዲስ ዓለማየሁ [ የሕብረተሰብ ሁኔታ ልብ ወለድ ሊቅ] ዳኛቸው ወርቁ [የሕብረተስባዊ ሕሊናዊነት ትንተና ሊቅ] ሆኖም ሥነ ጽሑፍ በሕብረተሰባችን ስለአልዳበረ የማንበብ ልማድ አልተለመድም፤ ከላይ ከተጠቀሱት በላይ አለ የሚባል ሥነ ጽሑፍ የለም፤ ከአለም ሕሊናውነታችንን የሚያዳብር ሳይሆን እንደገድል ማሚቶ የሊላ ሕብረተስቦችን ታሪካዊ ሄደት የሚያስተጋባ ነው። ሥነጽሑፍ የአንድ ሕብረተስበን ታሪካዊ ሄደት ከትውልድ ትውልድ የተላለፈውን ቅርስ በሥነ ጽሑፍ ዳብሮ ሲጻፍ ነው፤ ይህም ማለት የቃላት አገባብና የዕረፈት ነገር አሰካክ፤ የጽሑፉን ጥራትና ይዘት ጽንሰ ኅሳቡን የሕብረተሰቡን አጠቃላይ ሁኒታ አንጸባርቆ በከፍተኛ ደረጃ ተቀነባብሮ ሲቀርብ ነው። እንዲህ ያለውሁኒታ” እንዳይፈጠር በዘርዕ ያዕቅብ ፍልስፍና ላይ የተሰጠው አስተያየትና ትንታኒ እንደመረጃ በአጭሩ ለአንባቢ ይቀርባል።

 

በመጀመሪያ ባጭሩ ስለፍልስፍና ታሪክ ማቅረብ አስፈላጊ ነው። ፈላስፋ ሲመራመርና ሲፈላሰፍ የአለምንም ፍርሃትና የሕሊና ሽብር መሆን አለበት፤ ለዝና እና ለዉዳሲ ከሆነ ግን ፍልስፍና አይሆንም፤ ምክንያቱም ፍልስፍናው በመሰረቱ ዉዳሲና ውግዘት ስለሚሆን በተጨባጭ ያለዉንሁኔታ” አያመለክትም፤ለምሳሌ በአገራችን በሚያስፈራ ሁኒታ የመጽሐፍ ቅዱስ መምህር ነን ብለው በማስተማር ላይ የተስተማሩት ወንጌላዉያን ነን የሚሉ ፍልስፍና ዉስጥ ገብተው የሕብረተስቡንሁኔታ” ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በማገናኘት የጥንቆላ ስራ ሲሰሩበት በግልጽ ይታያል። የሰው ልጅ ክብሩ ተገፎ ዘሩ እንዲጠፋ ባአለበትሁኔታ” ላይ ተበዳዩን ተበድያለሁ ስለአለ ብቻ ያወግዙቷል፤ እንደ ቢተክርሲቲያንም ጠላት ተደርጎ የሚታየበትም ሁኔታ ተፈጥሮአል፤ ይህ በጉልህ የሚያሳየው ሕብረተሰቡ በምን ዓይነትሁኔታላይ እንዳለ ነው፤  ለምሳሌ በግሪክ ሕብረተሰብ ውስጥ ሶክራትስ የሚባል ፈላስፋከግሪክ ዉጭ የመጣ ጣዖትን ታመልካለህተብሎ በግሪክ ሕብረተ ሰብ ስለተወገዘ በሞት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል፤ በዚህም ምክንያት ሊዮንና ፕላቶ የተባሉ ፈላስፋዎችበግሪክ አስተዳደር ስርዓት ዉስጥ ሕሊናዉነቱ የዳበረ ሰው ሊኖር አይችልም ሲሉ ምስክርነታቸዉን ስጥተዋል። በአንፃሩ ደግሞ በማግና ካርታ [1215 .] ድንጋጌ መሰረት ንጉሡ ምንም እንኳ ንጉሥ ቤሆን ከሕግ በላይ መሆን የለብትም ስለተባለ የሰው ልጅ የሕግ ተገዥ እንዲሆን አስትዋፃኦ አድርጓል። ቀደምም ሲል የተጻፉ ጽሑፎች የሥነ ጽሑፍን ታሪካዊ ሄደት በሚገባ ያመለክታሉ፤ የሆመር ኢሊያድና ኦዲሲ ለግሪክ ሕብረተስብ ሥነ ጽሑፍ የመጀመሪያው ነው፤ ከጊታ ልደት በፊት አንድ ሺህ አንድ መቶ ዓመተ ዓለም የነበረው ሆመር በዝና የሚታወቀው በቅኔ አና በማኅሌት ነበር፤ጽሑፉም መወድስና ዜና መዋዕል ስለነበሩ የሚያንጸባርቁት አምስቱን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን ነው። ይህም ሆኖ የሆመር ጹሑፍ የግርኪን ሕሊናውነትን አያመለክትም፤ ሆመር ከባቤሎንያ ወደግሪክ የተሰደደ ስለሆነ የሚያንጸባርቀው የመጣበትን ሕብረተሰብ ነው፤ ይህ ከዚህ በላይ የተጠቀስው ምሳሌ ፈልስፋ ገደብ በሊለው ነፃነት ሲመራመርና ግኝቱን ለሕብረተሰቡ ሲያካፍል ሕልናዊነት ይዳብራል፤ መጥፎ ሁ”ኔታዎች” ወደ ጥሩ ሁኒታ ይለወጣሉ፤ እንግዲህ ይህ ከተባለ በኅላ ውይይታችን በተረጋጋ መንፈስና ደረጃውን በጠበቀ መከባበር ይሆናል።

 

ስለ ዘርዕ ያዕቆብ የተደረገው ውይይት ስለ “ፍልስፍናው” መሆኑ ቀርቶ መጽሐፉን ማን እንደጻፈው መሆኑ እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነው። የፕሮፊሰር ጌታቸው ኅይሌ ዋና ትኩረት ይህ ነው። ከሳቸው አስተያየት በፊት ግን በሙያ ፍልስፍናን ያጠኑ መምህራን የሰጡትን አስተያየት በአጭሩ ማቅረብ አስፈላጊ ነው፤ አነዚህ የኢትዮጵያ ፈላስፋዎች ራሳቸው በግዕዝ የተጻፈዉን መጽሐፍ ፈልገዉና መርምረው ሳይሆን ፕሮፈሰር ሳምነር ተርጉመውየጥንታዊ ፍልስፍና ታሪክተብሎ በታተመው መጽሐፍ ላይ የአደረጉቱን ርብርቦሽ ነው። ፈላስፋዎቹም ዶክተር ቀልቢሳ ወርቅነህ፤ ዶክተር አምባዮ ወንዲፍራው፤ ዶክተር መሳይ ከበደ እና ሊሎቹም ስለ ዘርዕ ያዕቆብ ሰፋ ያለ አስተያየታቸዉን ሰጥተዉበታል። እነዚህ መምህራን ምንም እንኳ ኢትዮጵያዉያን ቢሆኑ ዘርዕ ያዕቆብን የተመለከቱት በአውሮፓዉያን ዓይን ነው። የመምህራኑ አስተሳሰብ ባጭሩ የተመሰረተው በዘርዕ ያዕቆብ ችሎታና ፍልስፍና በተባለው ዝክረ ነገር ላይ ነው። የፈላስፋዎቹ መጀመሪያ ጥያቄ ፕሮፈሰር ሳምነር በምን ዓይነት መለኬያ ነው ዘርዕ ያዕቆብን ከፈረንሳዩ ፈላስፋ ደስካርትስ ጋር ማወዳደር የቻሉት? ደስካርትስ አውሮፓዉያን ስለሆነ በአስተሳሰብም ሆነ በፍልስፍና ከዘርዕ ያዕቆብ ጋር ሊወዳደር አይችልም የአውሮፓዉያን ርዕየተ ዓለም ከኢትዮጵያን ጋር የተለየ ከመሆኑም በላይ በሳይንስና በቴክኖሎጄ ብዙ ስለተራመዱ በእነሱ ደረጃ ያለ ዕውቀት ሌኖረው አይችልም ብለው በማሰብ ነው ዶክተር መሳይ ከበደየዘርዕ ያዕቆብ አስተሳሰብ መንፈሳዌ ስለሆነ እንደ ደስካርትስ ዓለማዌ ሆኖ ሌያስብ አይችልም፤”  ከዚህም በላይ ደግሞየአውሮፓውያን ሕሊና ንቃት ከኢትዮጵያውያን  ሕሊና ንቃት ጋር ሊወዳደር አይችልም፤ማለትም በፍልስፍና ደረጃ አንድ ስለአልሆኑ ይላሉ። በዚሁ መስመር ላይ አንድ በመሆን ዶክተር አምባዮ ወንዲፍራውየደስካርትስ ፍልስፍና ለዘርዕ ያዕቆብ እንግዳ ነገር ስለሆነ እንደሱ ፈላስፋ ነው ማለት ዘበት ነው፤ ፈጽሞ ዘርዕ ያዕቅብ ደስካርትን ሊሆን አይችልምበማለት ይደመድማሉ። እዚህ ላይ ፈላስፋዎቹ በትኩረት የተመለከቱት የአውሮፓውያንን ሳይንስና ቴክኖሎጄን ታሪካዌ ሄደት ነው። ነገር ግን ደስካርትና ዘርዕ ያዕቆብ ተመሳሳይ የሆነ የሥነ ፍጥረት አመለካከት አላቸው፤ደስካርት የሰው ልጅ ሁለት ፍጥረት አለው ብሎ ያምናል፤ አንድኛው ፍጥረት እግዚአብሒር በአምሳሉ የፈጠረው አካል ነው፤ ሁለትኛው ፍጥረት ደግሞ በስተንፋሹ እፍ ብሎ የፈጠረው ነፍስ ነው ይላል። ዘርዕ ያዕቅብ ደግሞ ፍጡር ያለ ፈጣሪ አይኖርም ይላል። ይህንን ያሉት በአንድ አካባቢ ዘመን ነው። አንዱ ከአንዱ ቀዳው እንዳይባል አንዱ ኢትዮጵያ ሊላው ደግሞ ፈረንሳይ ነው ያለው። ሁለቱም መንፈሳዌና ዓለማዌ ፈላስፋ መሆናቸውን አያጠራጥርም። ፍልስፍና አንድ የተወሰነ አገር የለውም። ሼክ አንታ ዲዮፕ የሚባል የአፍርቃ ሊቅ ስለፍልስፍና ሲጽፍ እንዲህ ይላል፤ፍልስፍና ማለት ማንነቱንና ሲያውቅና እውነትን እውነት ከአልሆኑ ነገሮች መለየት ሲችል ነውይላል።  ግሩም አባባል ነው። ይህም ሆኖ የኛ ፈላስፋዎች ፍልስፍናው ጠፍጧቸው ሳይሆን ትኩረት የሰጡት ሳይንስና ቴክኖሎጄው ስለሆነ ብቻ ነው። ሆኖም ዘርዕ ያቆብና ደስካርት በንጥረ ነገር የተደገፈ ያገኙት ፍልስፍና የለም። ነገር ግን ሥነ ፍጥረትን በሚገባ የመረመሩ ፈላስፋዎች ናቸው።

 

ወደ ፕሮፈሲር ጌታቸው ኅይሊ ትንተና ከመግባታችን በፊት የፍልስፍና  ዕውቀትን ምዕራብውያን እንዲት አድርገው ለሁለት ከፍለው እንደሚያዉት በአጭሩ መግለጽ አስፈላጊ ነው። አንባቢ እነዚህን ሁለት ክፍሎች በትኩረት ከመረመረ በፍልስፍና ላይ የሚደረገውን ውይይት ለመከታተል ይረደዋል ብዮ እገምታልሁ። እነሱም የአውሮፓዉያን ፍልፍስና እና የባንቱ ፍልስፍና ተብለው በትምህርቱ ገበታ ላይ ለአሉ ተማሪዎች በአልፉት አምሳ ዓመታት ዘመን ዉስጥ ጀምሮ ሲሰጥ የኖረ ትምህርት ነው። ተማሪዎችም በትጋት ተከታትለው የአለምንም ጥያቂ ተቀብለዉታል። ባንቱ ማለት ለጥቁር አፍሪቃ ቋንቋዎች በአንድነት የሚጠሩበት ስም ነው። ባንቱ የጥቁሮችን ሕብረተሰብ አጠቃሎ የያዘ ቋንቋ ነው፤ ለመጀመሪያ ግዜ የባንቱ ፍልስፍና በማለት የሰየመው ፕላሲድ ቴምፕል የሚባል ወንጌላዌ ክርስትናን ለማስፋፋት ከአውሮፓ ወደ አፍሪቃ አህጉር የሄደ ቄስ ነው። ቄሱም ክእግዚአብሒር የተላኩህ መልዕክትኛ ስለሆንክ አፍሪቃዉያን ትምህርቲን ተቀብለው እንድያምኑ ከላይ የተሰጠ ቃል ነው በማለት ፍልስፍና በባንቱ ቋንቋ ምን ማለት እንደሆነ አስተምሮአል። ይህንንም አፍሪቃዉያን አምነው ተቀብለዉታል፤ በቲምፕል አባባል በባንቱ ቋንቋ የሰዉነት አካልኅይልነው፤ ከሕሊናዊነት ጋር ምንም ግንኙነት የለዉም፤ እምነቱም ሕሊናብስነት ስለሆነ የሚጠቀመውኅይልንብቻ ነው፤ከኅይልዉጪ ሊላ ነገር አያውቅም ይላል። በአንፃሩ ደግሞ የአውሮፓውያን ፍልስፍና መሰረቱ ሕሊናዉነት ነው፤ የአውሮፓዉያን የሰውነት አካል ከሕሊናዉነት ጋር የተያያዝ ስለሆነ አይነጣጠሉም፤ ኅይሉም የሕሊንዉነቱ ተገዢ ሰለሆነ ሕሊናብስነት የለዉም በማለት ሁለት የተለያየ የፍልስፍና መዋቅር አስቀምጦልናል፤ የአውሮፓዉያን ፍልስፍና እና የባንቱ ፍልስፍና፤ ስለዚህ ነው ደስካርትና ዘርዕ ያዕቅብ አንድ መሆን አይችሉም የተባለበት።

 

እንግዲህ ከዚህ በላይ የተጻፈውን ሁለት የፍልስፍና ግብረ ኅይል ከመረመርን በኋላ እንዲት ሊሆን ይችላል ብለን መጠየቅ ግዴታ ነው፤ ይህን ጥያቄ መጠየቅ ከአልቻልን አውሮፓውያኖች እንድሚሉት እውነትም ሕሊናቢስ ነን ማለት ነው። በመሰረቱ ይህ ሊሆን አይችልም፤ፍጥረት አንድ ነው፤ የሰው አካልና ሕሊናው አይለያዩም። ለዚህም በቂ መረጃ ሆኖ የሚሰጠው የታላቁን አፍሪቃዌ ፍልስፍና ታሪክ ነው። የዚህ ታላቅ ፈላስፋ ታሪክ የሚጀምረው በትንሽ ቦታ አክሲም በምትባል መንደር ነው። አክሲም የምትገኝው በምዕራብ አፍሪቃ ጋና በሚባለው አገር ዉስጥ ነው፤ የፈላስፋው ስምአሞይባላል፤ የተወለደውም 1700 አካባቢ ነው ተብሎ ተገምቷል፤ ጀርመን አገር የሚገኝ ብረንዊስክ ዎልተንባትል በሚባል ቤተክርስቴያን መዝገብ ዉስጥ ተጽፎ የሚገኝው ሰነድ እንደሚያመለክተውአንቶን ዊልሃልም አሞተብሎ 8 ዓመቱ ክርስትና ተነስቷል።አሞከአፍሪቃ ወደጀረመን እንዲት እንደተወሰደ በጽሑፍ የሚታወቅ ነገር የለም፤ ሆኖም ክርስትናዉንም ሆነ ትምህርቱንም  የተከታተለው አንድ የጀርመን መስፍን ቤት ዉስጥ ሆኖ ነው፤ አንዳንድ ታሪክ ጸሐፊዎች እንድሚሉት የብረንስዊክዎልፈንባትል መስፍንአሞንን”  ከጋና ያስመጣው ቅስና ተቀብሎ ክርስትናን አፍሪቃ ዉስጥ እንዲያሰተምር ነው ይላሉ፤ ነገር ግን በጽሑፍ የተገኝ መረጃ የለም።አሞንበመስፍኑ ቤት እንደቤተሰብ ሆኖ በታላቅ እንክብካቤ ጀርመን ዉስጥ አሉ ከተባሉት ታዋቄ ትምህርት ቤቶች በመከታተል በታላቅ ማዕረግ ትምህርቱን አጠናቋል፤ በቋንቋም ልዩ ስጦታ ስለነበረው የተለያዩ የአውሮፓዉያን ቋንቋዎች አጥንቷል፤ የመጨረሻውንም የፍልስፍና ዶክቴሪት የጻፈው በላቲን  ነው። እንግዲህአሞንንታላቅ ከአደረጉት ውስጥ ሁለቱ የፍልስፍና ጽሑፎች ናቸው፤ አንደኛውና ታዋቂው ጽሑፉስሜት በሕሊና ሳይሆን በአካል ዉስጥ ይገኛልበማለት የጻፈውንጥረ ነገርነው፤አሞበታላቅ ደረጃ ተመራቂ ስለሆነ ታዋቄው በሆነው ሔል ዩነቨርስቲ በፕሮፊሰርነት ማዕረግ ተቀጥሮ በሚያስተምርበት ግዜ ለተማሪዎቹ የሚያስተምረው ስለ ቁሳዊ አካልና ሒሊና ባሕራያት ነበር፤ ይህም ትምህርቱ በተማሪዎች ዘንድ ታላቅ አክብሮትን አስገኝቶለት ነበር። 1738 ባቀረበው ጽሑፉበተረጋጋ  መንፈስ የሚጻፍ ትክክለኛ ፍልስፍና”  በማለት ሽፍጠኞችን ዘረኞችንና  የኃይማኖት አክራሪዎችን በሚገባ ተችቷል፤ የፈረንሳዊውን ፈላስፋ ደስካርት የጻፈውንሁለት ፍጥረትበመቃወም ስለ ቁስ አካል ታሪካዊ ሄደት በንጥረ ነገር አስረድቷል። ስለ ቁስ አካልም ሲፈላስፍ እንዲህ ይላልያለ ነገር ይኖራል፤ ሊኖር የሚችለውም በእንክብካቤ ነው፤ ለእድገትም እንክብካቤ ያስፈልገዋል፤ እነዚህ ሁሉ መሆን የሚችሉት ይህሁኔታ” ሲፈጠር ብቻ ነውይላል።ሁኔታየሚለውየአሞ”  ሁለትኛውንጥረ ነገርነው።አሞበጀርመን ፍልስፍና ታሪክ ዘመን ሁለትንጥረ ነገሮችንየጻፈ ብቸኛው ፈላስፋ ነው። ይህም ሆኖ ያሳደገው መስፍን ስለሞተ በፍልስፍናው ደስተኛ ያልሆኑ የኃይማኖት አክራሪዎች ከሚያስተምርበት ወንበር አስነስተው ከአገር እንዲባረር አድርገዋል።አሞወደ ትውልድ አገሩ አፍሪቃ ተመልሶ ብዙም ሳይቆይ በተወለደ 56 ዓመቱ አርፏል።አሞተወዳዳሪ የሊለው ታላቅ ፈላስፋ ነው። አውሮፓውያን ሊላዉን ሕሊናቢስ ማለት አይችሉም።የአሞትምህርት ጀርመንም ሆነ ሊላ አገር አፍሪቃዉነቱንና ሕሊናዉነቱን አይቀይረውም፤ ሰው ስለሆነ ሰው የሚያደርገዉን ሁሉ የማድረግ ፉጡራዊ ሕግ ስለሆነ ነው፤ ይህ የተባለበት ምክናያት አንባቢ ይህንን አስታውሶ ለወደፊቱ ውይይታችን እንዲረዳው ይጠቅማል በማለት ነው።  

  

አሞእንደሚለው ፍልስፍናበተረጋጋ መንፈስና በትክክልመጻፍ አለብት፤ ይህም ማለት ፍልስፍና አውነትና ትክክል ነው፤ በተጨማሪ ፍልስፍና ለሰው ልጅ ጠቃሚ ነው፤ ለሰው ልጅ ጠቃሚ ከአልሆነ ግን በሁለተኛው ጽሑፉ ላይ እንደገለጸውሸፍጠኛ” “ዘረኛ” “ወገንተኛይሆንና ለስው ልጅ አጥፊው ይሆናል። ለምሳሌ አሁን ኢትዮጵያ ባለችበት ሁኒታ አንድ ታጋይ ሲፈላስፍ እንዲህ ይላል፡እኒ የምታገለው አማራን መልሼ ሥልጣን ላይ ለማውጣት አይደለም የአማራ ገዥነት በዘመነ ጉጉግ ማንጉግ ጌዜ የኢትዮጵያ ወጣት ተማሪዎችበሽፍጠኛ ፈላስፋዎችገና በእንጨቅላነታቸው በተጠለፉበት ዘመን የተወራ ወሬ ነው፤ የጄሬናል ቫረቴሌ የዱቼ ሙሰሌኔ የቫንዳ የልጅ ልጆችና አሽከሮቻቸው ፕሮፓጋንዳ ነው።  አሁንም እነኛሽፍጠኛ” “ዘረኛእናወገንተኛፈላስፋዎች ለእናት ኢትዮጵያ የሞቱላት ጀግኖች እየተባለ ዝክረ ነገራቸው ሲነገር የሚያሳየው አንድ ሕብረተሰብ ሊቆጣጠር ከሚችለው በላይ ሆኖበት ኅዘኑን ከመግለጽ በላይ ያለበትንሁኒታሊያቀውም ሊለውጥም  አለመቻሉን ነው–“አገሪ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፤ የሞተለሽ ቀርቶ የገደለሽ በላእያለየሁኒታ ተገዥሆኖ ቀርቷል። ልጆቿን የገድሉ ነፈሰ ገዳዮች ዛሪኢትዮጵያ አገሬ እንሞትልሽናል እንስባበርልሻለንእያሉ ሲዛበቱባት ማየት አስገራሚ ነው። ዕውነትን ያልተከተለ ፍልስፍና ሕበረተሰብን ያጠፋል፤ በመለስ ዚና እና በኢሳእያስ አፈወርቂ ልዩ ትዕዛዝ የአማራ ሕብረተስብ እንደበግ ታርዷል፤ በገደል ክእነፍሱ ተወርዉሯል፤ ገበሪው ሲቱ ሽማግሊው ሕፃናቱ እቢቱ ዉስጥ ቷጉረው በእሳት ነድዋል። መለስ ዜናዌ በለሐጩ ያዝረከረከው መርዝ ደግሞ እንደራዕይ ተቆጥሮ ይነገርለታል። የጀርመኑ ሄትለር ይሁዲዎችን በጋዝ ሲያቃጥል ለሰው ልጅየመጨረሻው መፍትሄብሎ ነው፤ ግን ይሁዲ ሰው ስለሆነ የእሱ ጥፋት ደግሞ እንደመፍትሄ ከሆነ የሰው ልጅ ሁሉ መጥፋት ይኖርበታል፤ ይህ ከአልሆነ ግን መፍትሄ ያለው ሊሆን አይችልም። ጥራት የሊለውየወገንተኛ ፍልስፍናየሚባለው ይህ ነው፤ ትልቅ የፍልስፍና ድሕነት፤ ግብዝነትና ጨቃኝነት። ማከቬሌ ሥልጣን ለመያዝ የተጠቀመው ፍልስፍና የሰውን ልጅ ሰብአዌ  መብት በመጣስ ነው፤ ገድሎም አታሎም ሰርቆም አስሮም ሥልጣን መያዝ ተገቤ ነው ስለሚል ሕብረተሰቡን አሳምኖ ተቀባይነት እንዲያገኝ አድርጓል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ለአልፉት አንድ መቶ ዓመታት በሥልጣን የወጡ አምባገነኖች ገድለው አስረውና አታለው ነው። ከላይ የተጠቀሰው ሰው የሚታገለው ለሥልጣን እንጂ አገርን ነፃ ለማውጣት አይደለም። በዚሁ አይነት የሥነ ምግባር ፈላስፋዎች የፈልስፉትን አቶሚክ ቦምብ አገልግሎቱ ለሰው ልጅ እድገት ብቻ እንዲሆን ከመንግስት ጋር ለማድረግ ያቀዱት ውይይት ሊሳካ አልቻለም፤ከግኙቱ በሗላ አጠቃቀሙን የሚወስነው መንግስት እንጂ ሊላ አካል ያለመሆኑን ሲያውቁ የተፈጠረውሁኒታከቁጥጥራቸው ውጭ ስለሆነ የፍልስፍናው ዉጤት ጥፋት ሆነ። በዚህ ፍልስፍና የተግኘ ግኝት ልክ የዛሪ 70 ዓመት ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ሕዝብ በሆሮሽማና በናጋሴ ከተማዎች እንዲጠፋ ምክናያት ሆኗል። ጥራት የሊለው ፍልስፍና የሚያስክትለው ጉዳት የቱን ያህል እንደሆነ አንባቢ በአንክሮ እንዲመለከተው ያስፈልጋል። በዘመኑ የዘርዕ ያዕቆብን ፍልስፍና ሊቃዉንቱ በተርጋጋ መንፈስ ቢወያዩበት ኖሮ ምናልባት ሕብረተሰባችን አሁን ያለበት ሁኒታ ዉስጥ ላይኖር ይችል ነበር ብዮ እገምታለሁ፤ ይህ እንደ መላ የተሰጠ ግምት ነው። 

 

እንግዲህ የፍልስፍናን ትርጉሙን ታሪካዌ ሄደቱን ጥቅሙን እና ጉዳቱን በአጭሩ ከተመለከትን በኋላ የፕሮፈሰር ጌታቸው ኅይሌንሐተታ ዘዘርአ ያዕቆብበሜል መቅድም ላይ የሰጡትን አስተያየት በአንክሮ እንመለከታለን። ቀደም ብሎ እንደተጠቀሰው አስተያየታቸዉን ለማረም ሳይሆን በዘርዕ ያዕቆብ ፍልስፍና ላይ የተደረገዉን ውይይት በተመለከተ ይሆናል። ፕሮፈሰር ጌታቸው ኅይሌ በአስተያየታቸው መቅድም ላይ የጻፉት በሶወስት ደረጃ ተከፍለው በተሰጡት ደንብ መሰረት አይደለም፤ ይህ ደንብ የዜህ ጸሐፊ ሳይሆን የሥነ ጽሑፍ መሰረታዌ መነሻ ነው። አንባቢ በትኩረት ተመልክቶ ከሳቸው ጽሑፍ ጋር አመሳክሮ ምስክርነቱን ሊሰጥበት ይገባል፤ በአንደኛ ደረጃ ማየት ያለብን መጽሐፉ ባለቤትም አርዕስትም አለው። ፕሮፈሰር ጌታቸው ኅይሌም ይህንን እንደሜቀበሉ አምናለሁ፤ በዚህ ላይ ከተስማማን በዘርዕ ያዕቆብ ፍልስፍና ላይ የአደረጉት ውይይት የሚጀምረው እንዲህ በማለት ነው፡

 

 

ሐተታ ዘዘርአ ያዕቆብ በሚባል ስም የሚታወቀው የወርቄ የሕይወት ታሪክ

 

መቅድም

 

አንድ ጁስቶ ኡርቢኖ (Padre Giusto da Urbino) የሚባል

የካቶሊክ ሚሽኔሪ ደብረ ታቦር (ደምቢያ) ላይ ሆኖ በፌብሩዋሪ 1853

..(=1844..) የአንድ የግዕዝ ድርሰት ሁለት ቅጂዎች በዚያን

ጊዜ ፓሪስ ለሚኖረው አንቷን አባዲ (Antoine d’Abbadie)

ይልክለታል። አንቷን .አባዲ በዘመነ መሳፍንት ኢትዮጵያ መጥቶ ዛሬ

ከታላቁ የፓሪስ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ካሉት የግዕዝ መጻሕፍት

አብዛኞቹን ሰብስቦ ያመጣ ተመራማሪ ነበር። አንቷን .አባዲ እነዚህን

ሁለት ቅጂዎችም በዚያው በታላቁ ቤተ መጻሕፍት ከትቷቸው፥

አንደኛው በስሙና በቊጥር፥ D’Abbadie 215 ሁለተኛው

D’Abbadie 234 በመባል ይታወቃሉ። .ሐተታ ዘዘርአ ያዕቆብ.

የሚባለውን የኢትዮጵያ ጥናት ሊቃውንትን ያጨቃጨቀውን የወርቄን

የፍልስፍና ትችት የያዙ እነዚህ ሁለት ቅጂዎች ናቸው።

ጭቅጭቁ ምን እንደሆን ያልሰማ እንዳለ፥ በአጭሩ እንዲህ ነው፤ ይህ

ድርሰት በዓሥራ ሰባተኛው ምእት ዓመት የኖረ ዘርአ ያዕቆብ የሚባል

ኢትዮጵያዊ የደረሰው አይደለም፤ ፓድሬ ጁስቶ ኡርቢኖ (Padre

Giusto da Urbino) ሚሲዮናዊ ስለሆነ ማንነቱ እንዳይታወቅ .ዘርአ

ያዕቆብ. የሚል የብዕር ስም አውጥቶ የደረሰው ነው የሚል ነው።

ቅጂዎቹን ሊያያቸውና ሊመረምራቸው የሚፈልግ መታወቂያቸውን

ጠቅሶ ፎቶግራፋቸው ከፓሪስ እንዲላክለት መጠየቅ ይችላል።

ጭቅጭቁ የተካሄደባቸውን ምንጮች ከዚህ ጽሑፍ መጨረሻ

ዘርዝሬያቸዋለሁ።

 

ፕሮፊሰር ጌታቸው ኅይሌ በምን ምክናያት “ሐተታ ዘዘርአ ያዕቆብ” የሚለውን መጽሐፍ በጁስቶ ዳ አርቢኖ አማካይነት የሚጀምሩት? ፈረንሳዩ አንቷን ዳ አባዲ በአባሪነት የቀረበበት ምክናያት ለምንድነው? ደግሞስ “የኢትዮጵያ ጥናት ሊቃዉንት [የዉጭ አገር መምህራን መሆን አለባቸው] ያጨቃጨቀዉን” የሚሉት? ምን አገባቸው በኢትዮጵያ ፍልስፍና ላይ? ለምንስ ወዳጃቸው አቶ አሰፋ ገብረማርያም እንደጠየቁት ትርጉሙን ተርጉመው ለአንባቢ አያቀርቡም ነበር? አንባቢ ከላይ በአባሪነት የቀረበውን መረጃ ተመልክቶ አስተያየቱን ሊስጥ ይችላል፤ ሆኖም ከዚህ በላይ የተጠቀሰው ለዘርዕ ያዕቆብ ፍልስፍና መጽሐፍ መነሻ ሊሆን አይችልም፤ መነሻ ሊሆን ቀርቶ በዋቢነት መቅረብ አይችልም፤ ምክናያቱም መረጃ የሊለው ወሬ ነው።በተጨማሪ ከላይ በአጭሩ እንደተማርነው ፍልስፍና “በጭቅጭቅ “ አይገኝም፤ ፕሮፊሰሩ የቋንቋ መምህር ስለሆኑ የሽሎታ ማነስ ሳይሆን የቃላት  አመራረጥ ክስተት ይሆናል ብዮ እገምታለሁ፤ ፕሮፊሰር ጌታቸው ኅይሌ በመቅድማቸው መነሻ አድርገው የሰጡ መሰረተ ቢስ ከመሆኑም በላይ የአንድ ቅርስና ባለቤትነትን የሚጻረር ነው። ለዚህም መረጃ የሚቀጥልውን ትንተና በትኩረት ይመልከቱ፡

 

 

                        ከዚያም አልፎ ተርፎ፥ ድርሰቱ በክርስቲያኖች ዓይን ሲታይ ህርጥቅና

                      (heresy) ስለሆነ፥ .እንዳልታወቅ ዘርአ ያዕቆብ በሚል በብዕር ስም

                      የጻፍኩት እኔ ነኝ. ሳይል አልቀረም። የጻፈው ማስታወሻ ተገኘተብሎ፥

                      በካርሎ ኮንቲ ሮሲኒ መሪነት ድርሰቱ ከዘርአ ያዕቆብ (ከወርቄ

                      ማለት ይሻላል) ተወስዶ ለጁስቶ ኡርቢኖ ተሰጠ። ሌሎች

                      ተመራማሪዎችም፥ በተለየም ኦይገን ሚትቮኽ (Eugen Mittwoch)

                       የኮንቲ ሮሲኒን ፍርድ አጸኑ። ፓድሬው በወርቄና በድርሰቱ ላይ

                    ያደረሰውን በደል እስከዛሬ ከሊቃውንቱ አእምሮ መፋቅ አልተቻለም።

                        የኮንቲ ሮሲኒ አቋም ኢትዮጵያውያንን አስቆጣ። የዘርአ ያዕቆብን ስም

                        ሰምተው የማያውቁ ሁሉ ፈላስፋ ነው ስለተባለ ብቻ ኢትዮጵያዊ

                        እንደነበረ መሰከሩለት።

 

 

ፕሮፊሰር ጌታቸው ኅይሌ ትኩረታቸው ትርጉሙ ላይ ስለሆነ የዘርዕ ያቆበን ሐተታ በሚገባ ተመልክተዉታል ማለት ያስቸግራል፤ ትርጉሙን ከጨረሱ በኋላ በቀጥታ ወደራሳቸው አስተያያትና በጽሑፉ ላይ ዕውቀት አላቸው የሚሏቸውን ሊቃውንት ትንትን ውስጥ የገቡት፤ በመጀመሪያ የዘርዕ ያዕቆብ ጽሑፍ መታየት ያለበት በሊላ ዓይን ሳይሆን በርሳቸው መሆን ነበረበት፤ እሳቸው እንዳሉት “ህርጥቀኛ” [ሃይማኖተ ቢስ] የሆነበትን ምክንያት ከመጻሐፉ ጠቅሰው ለመረጃ እንዲሆን ማቅረብ ነበረባቸው፤ ግን ወሪ ሰምተው “ህርጥቅና” [ሃይማኖተ ቢስ] ያሉት፤በሥነ ጽሑፍ እንደዚህ ዓይነቱ ክስተት አይፈቀድም። ሁለተኛ ዘርዕ ያዕቅብ ስለ ሃይማኖቱ ሲመራመር እራሱን እንደ “ህርጥ ቅና” [ሃይማኖተ ቢስ] አድርጎ አልተመለከተውም፤ አንባቢ በትኩረት መመልከት ያለበት ፕሮፊሰሩ ዘርዕ ያዕቆብ የጻፈው “ሐተታ” በደንብ አድርገው እንዳልተመለከቱት ነው፤ በጽሑፉ ያልተስማሙ ደብተራዎች “ህርጥቅና” [ሃይማኖተ ቢስ] ነው ስለ አሉ ምናልባት ሳይሆን አይቀርም በማለት ነው የደመደሙት፤ ካርሎ ኮንቲ ሮሲኒ እና ሚቶቮኽ ያሏቸው ሊቃውንት ለምን በዋቢነት እንደተጠቀሱ ግልጽ ነው። እነዚህ የውጭ አገር ሊቃውንት ለእኛ ኢትዮጵያውያን ለዕውቀታችን መለኪያ አድርገን ስለምንመለከታቸው

የእነሱን ስም ዋቢ አድርገን መጥራት ግዲታችን ስለአደረግነውና ስማቸው በዋቢነት ክአልተጠቀሰ ውይይቱ ዋጋ ሊኖረው አይችልም ብለን ስለምናምን ነው። መጽሐፉ ከተጻፈ ሁለት መቶ ዓመት በኋላ የውጭ አገር ሊቃውንት ወደአገራችን መጥተው በአገሪው ሰው የተጻፈዉን መጽሐፍ ጻፈው አልጻፈው ማለት ብቃቱ እንደሊላቸው ስለማናውቅ ብቻ ነው። ፕሮፊሰሩ ከሁለቱም ሊቃውንት በበለጠ ስለአገራቸው ዕውቀት አላቸው ብዮ እገምታለሁ። ነገር ግን የእነዚህ ሊቃውንት ስም  መጠቀስ የሳቸውን ዕውቀት ከፍ ያደርገዋል ተብሎ ስለሚገመት ነው እንጂ ዘርዕ ያዕቆብ የተመለከተውን የአገሩን “ሁኒታ” እነሱ በበለጠ ያውቁታል ማለት አይደለም። ፕሮፊሰሩ ይህንን “ሁኒታ” በአንክሮ ተመልክተው ማወቅ ግዲታ ነበር። በእርሳቸውም ዘመንም ሆነ  በአሁኑ ታዋቂ የውጭ አገር ሊቃውንትን በዋቢነት ማቅረብ ዕውቀታችንን ከፍ ያደርገዋል ብለን ስለምናስብ ነው። እዚህ ላይ አንባቢ መመምልከት ያለብት ታዋቂ ሊቃውንት አይጠቀሱ ማለት ሳይሆን ሥራዓትን ተከትሎ ይሁን ለማለት ነው። ግን እንደጡት እናትና አባት ሆነው ሁሉንም ነገር እነሱ እንዳሉት ማለት ገደብ የሊለው ጥገኝነት መፍጠር ይሆናል። በአጭሩ ኮንቲ ሮሲኒ በዘርዕ ያቆብ ጽሑፍ ላይ አስተያየትም ሆነ ትችት የማድረግም ብቃትም  ሆነ ችሎታ የላቸውም፤ ወደአገራችን የመጡት የተልያዩ ቋንቋችንን አጥንተው ልዩነታችንን አጉልተው ለማሳየት ነው። በተጨማሪ አንድ የኢትዮጵያ ደብተራ እንደዚህ ዓይነት ጽሑፍ ሊጽፍ ብቃት የለዉም በለው ስለሚያምኑ ጸሐፊው አውሮፓውያን ሳይሆን አይቀርም በሚል መላ ምት ያወሩት ወሬ ነው። ወሬ በዋቢነት ሊቀርብ አይችልም፤ ፕሮፊሰር ጌታቸው ኅይሌ  እዚህ ላይ ሊስማሙ ይገባል።  

 

ፕሮፊሰር ጌታቸው ኅይሌ ስለ ዘርዕ ያቆብ ፍልስፍና ምን ለማለት አስበው እንደሆነ ላማወቅ አስቸጋሪ ነው፤ “የኮንቲ ሮሲኒ አቋም ኢትዮጵያንን አስቆጣ ………..ዛሬ የዘርአ ያዕቆበን ሰምተው የሚያውቁ ሁሉ ፈላስፋ ነው ስለ ተባለ ብቻ ኢትዮጵያዊ እንድሆነ መሰከሩለት” ይላሉ፤ ደግሞ በትንትናቸው ላይ “ድርሰቱ በክርስቲያኖች ዓይን ሲታይ ህርጥቅና” ነው ይላሉ፤ ጽሁፋቸው ጥራት የለዉም፤ ግደየለሽ ይታይበታል፤ቀደም ብሎ እንደጠቀሰው በዘመናዊ ትምህርት የተማሩ ኢትዮጵያዊያን ፋላስፋዎች አቋሟቸው ከኮንቲ ሮሲኒ አይለይም፤ ዘዕር ያዕቆበ የመጻሕፉ ደራሴ መሆኑን የሚያጠራጥር አይመስለኝም፤ ፕሮፊሰሩም በዚህ ይስማማሉ፤ ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ እና አቶ ዓለማየሁ ሞገስ የኮንቲ ሮሲንን ወሬ በመቃወም የዘር ያዕቆብን ጸሐፊነት አረጋግጠዋል፤ ደግሞም አንድ ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ ሲገኝ የአገር ሕሊናዊነት ስለሆነ የወሰዱት አቋም ትክክል ነው፤ በአንፃሩ ፕሮፊሰር ጌታቸው ኅይሌ የዘርዕ ያዕቆብን ፈላስፋነት ለማመን አጥብቀው የተቸገሩ ይመስላሉ፤ ምክናያታቸውንም ሲሰጡ እንዲህ ይላሉ፤

 

 

 

 

 

 

 

 

ፍልስፍናው በመሠረቱ የሱ መሆኑን ግን በሁለት ምክንያቶች

እጠራጠራለሁ። አንደኛ፥ ተፈላስፎ የእግዚአብሔርን መኖር ያመነው፥

የሚያየው ፍጡር ሁሉ ያለፈጣሪ አይፈጠርም ከማለት ተነሥቶ ነው።

ይኸንን ከቅዱስ ቶማስ አኩይናስ (Thomas Aquinas, 1225-1274)

     ጀምሮ በካቶሊኮች ዘንድ የገነነ .ምክንያትና ውጤቱ. (The law of

causality) አስተሳሰብ ወርቄ የካቶሊኮቹ ተማሪ በነበረበት ጊዜ

አልሰማውም ማለት ያስቸግረኛል።

 

ከላይ በአጭሩ ስለ ፍልስፍና ስለተወያየን አሁን አዲስ ነገር አይሆነብንም፤ የፕሮፊሰር ጌታቸው ኅይሊም መጠራጠር አያስደንቅም፤ ይህ ትክክለኛ አቋማቸው ነው። ለውይይት ያህል እንደገና “አሞ “ የተባለዉን የጋናዉን ፈላስፋ መጥቀስ አስፈላጌ ነው። “አሞ” በሕፃንነቱ ከአገሩ ወደ ጀርመን ሄዶ ታዋቂ ፈላስፋ ሆኗል፤ ይህም የሚያሳየው  የተመቻቸ  “ሁኒታ” ስለአገኝ ተመራምሮ እንደደረሰበት አካሉ ከሕሊናዉነቱ ጋር ተባብሮ “ንጥረ ነገሮችን” በማግኝቱ ታላቅ ከተባሉት ፈላስፋዎች አንዱ መሆኑን አረጋግጠናል፤ “የአሞ “ አካልና ሕሊናዊነት የአፍርካም የጀርመንም አይደለም፤ የሰው ልጅ አካልና ሕሊና ነው፤ ይህ ፍጥረት ስለሆነ ማንም ሊወስደው አይችልም፤ ዘርዕ ያዕቆብና ቶማስ አኩይና ሰው ስለሆኑ ፍጡራዊ የሆነ አካልና ሕሊና አላቸው፤ ሃይማኖታቸው ተዋሕዶም ሆነ ካቶሊክ የአካልና የሕሊና ለዉጥ አያመጣባቸውም፤ “ሁኒታ” ግን ትልቅ ልዩነት ያመጣል፤ ለምሳሊ ዶሮ እንቁሏሏን ተንከባክባ አስፈላጌዉን ሙቀት ከአልስጠች ጯጩቶቹ አይፈልፈሉም፤ ፕሮፊሰሩ የሁለቱን ፈላስፋዎች “ሁኒታ” መርመረው ግኝታቸውን ቢሰጡን ኖሮ ጥሩ ነበር፤ ይህንን አላደርጉም፤ ያደረጉት እንደሊሎቹ ኢትዮጵያውያን ፈላስፋዎች ዘርዕ ያዕቆብ አውሮፓዉያን ሰለአልሆነ ሊፈላሰፍ  አይችልም ነው፤  በፕሮፊሰሩ አስተሳሰብ

ዘርዕ ያዕቆብ የሚያንጸባርቀው  ሃሳብ ከአምስት መቶ ዓመት በፊት የነበረዉን ዝነኛ  ፈላስፋ ቶማስ አኩይናን ነው ይላሉ፤ ፕሮፊሰሩ በዚህ ላይ የአላቸው አቋም ጠንካራ ነው፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ አሉ የተባሉ ታላላቅ መጻሕፍት ሁሉ ከውጭ በትርጉም የተገኙ ናቸው በማለት አጠንክረው ስልሚያምኑ ፍልስፍና   ለኢትዮጵይዉያን እንግዳ ነገር ይመስላቸዋል። ለዚህ ነው አጥብቀው የተጠራጠሩት። “ሁኒታ” ወሳኝ ነው፤ ስለዚህም ነው ዘርዕ ያዕቆብ በብዕር ስም ተደብቆ ጽሑፉን የተወልን፤ ነገር ግን ይህንን “ሁኒታ” ከግንዛቤ አስገብቶ “ሁኒታን” መቀየር ሲገባ ውይይቱ ሊላ ሆነ፤ እንግዲህ እንዲት ሆኖ ነው “ሁኒታ” ሊስተካከል የሚችለው? ከየትኛው መጽሐፍ እንደሆነ ባላስታውስም ጽሑፉ ግን ከአእምሮዮ አለ፡ መጽሐፉ እንዲህ ይላል “ወርኢኩ ጽሑፍ በላዕሊሆሙ እስመ ትውልድ ትኢብስ እስከ ትትነሣእ ትውልደ ጽድቅ ወአበሳ ትትኃጉል ወኃጢአት ትትለሑሱ እምዲበ ምድር ወኩሉ ሠናይኢ ኢይመጽእ።” “ጻድቃንና ብሩክ የሆነ ትውልድ እስኪመጣ ድረስ ጥፋት ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተልስለፋል፤ ግን መልካሙ ትውልድ ሲነሳ በምድር ላይ የአሉ መጥፎ ነገሮች ተወግደው መልካም “ሁኒታ” ይመጣል” [ትርጉሙ ቃል በቃል አይደልም]። እዚህ ላይ አንባቢ በአንክሮ መመልከት ያለበት ዘርዕ ያዕቆብ የአለንበትን “ሁኒታ” በተለያየ መንገድ ሲነግረን መስማት አልቻልንም። እዚህ ላይ ፕሮፊሰሩ “የሁኒታ” ጉዳይ መሆኑን ስለአልተገነዘቡ  “ሁኒታን” ለመለወጥ ምንም ያደረጉት አስተዋፃኦ የለም። መልካሙ ትውልድም መቺም እንደሚመጣ አይታወቅም፤ ነገር ግን አኛ የምናውቀው ትውልድ አጥፊ ትውልድ ስለሆነ ፍልስፍናዉም ጉግ ማንጉግ ነው፤ በዘመናችን የነበርንበትን “ሁኒታ” እንለውጣለን ተብሎ ወደ ባሰ መጥፎ “ሁኒታ” ገብተናል። የዚህ ታሪክ በአጭሩ እንደዚህ ነው፤  

 

ይህንን “ሁኒታ” ለመግለጽ ሰፊ የሆነ ጥናት ያስፈልጋል፤ ነገር ግን ለዚህ ውይይት ይረዳል የተባሉትን በአጭሩ መጥቀስ አስፈላጊ ነው፤ የኢትዮጵያ አገራችን ታሪክ ማለቂያ የሊለው “ሁኒታዎች” ከቁጥጥር ዉጭ ሆነው የሆነውንና የአልሆነውን ነገር ሲነገርባት የኖረች አገር ነች፤ ጥንታዊት ነች ግን የጥንታዊነታ ቅርስ አልተጠበቀም፤ በተለያየ “ሁኒታ” ጠፍቷል፤ በታሪክ ከ3ት ሺህ እስከ አንድ መቶ ዓመት ነው ተብሎ ተገምቷል፤ ግን 3ት ሺም አንድ መቶም  የሚሉ “ሁኒታዎች” ስለሚፈራረቁ በትክክል የታሪኳ ዘመን አይታወቅም፤ ክርስትናን በአገር ደረጃ የተቀበለች የመጀመሪያዋ ነች ይባላል፤ ነገር ግን አገልግሎቷ ለፖለቲካ አካል ስለሆነ ክርስትናን የሚያመለክት ምንም ነገር የለም፤ ፕሪስትር ጆን የሚባል ፋላስፋ ንጉሥ የሚገዛት አገር ስለነበረች ፍትሕ የሞላቧት ነች ይባላል፤ ነገር ግን የአምባ ገነኖች መጨፈሪያ ስለሆነች ፍትሕ ናፋቂ ሆና ቀርታለች፤ ከሁሉ የሚበልጥ ታሪክ አለን ብለን እናምናለን፤ ነገር ግን በምን ከሊላው እንደምንበልጥ የምናሳይበት ነገር የለም፤ ለምንስ ከሊላው መብለጥ እንዳለብንም አናውቅም፤ ለምንስ እንደሊላው  ጢነኛ ሰው አንሆነም? መብለጥስ ለምን አስፈለገ? ከሁሉ በላይ ክርስቲያን፤ ከሁሉ በላይ አዋቂ፤ ከሁሉ በላይ ኮሚኒስት መሆን አስፈላጊ ነው? እንደዚህስ ያሉ “ሁኒታዎች” ለጢንነታችን ጥሩ ነው? በእንደዚህ የአለ ታሪክ “ሁኒታዎች” የሚፈራረቁባት አገር ነች፤ ለመረጃ ከ1970 እስክ 1991 የተደረጉትን “የሁኒታ” ለዉጦችን መመርመር ጠቃሚ ነው። ጠቃሚነቱም ኢትዮጵያ በረጅም  ታሪኳ ለመጀመሪያ ግዜ የጎሳ ኮሮጆ እንድትሆን የተደረገበትን “ሁኒታ” መፈጠሩን ነው። ቤነዚህ ሃያ ዓመታት ዉስጥ የተደረጉት “የሁኒታ” ሄደት በታሪክ አጋጣሜ ሳይሆን በስሊት ተቀነባብሮ የተፈጠረ ነው። ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዚ የአውሮፓውያንን የጦር ኅይል ተቋቁማ ድል ስለናሳች መቀጣት አለባት በማለት የተነሱ ኅያላን መንግሥት ሴራ ነው አሁን ያለንበትን “ሁኒታ” የፈጠረው፤ የጂሪናል ቫረተሪ ሕልም እውነት የሆነበት “ሁኒታ” ፤ በአደዋ ጦረነት ግዜ የሚኒልክ ጦር በጎሳ ፍርክስኩሱ ይወጣል እያለ ስያልም ነው “የኦሮሞ ፈረስኛ” ድርምጥማጡን ያጠፋው፤ ስለዚህ ነው ኦሮሞ የኢትዮጵያ አካል አይደለም የተባለው? ስለዚህ  ነው የአማራ ዘር መጥፋት አለበት ተብሎ የተፈረደበት፤ በአጭሩ የሆነው እንዲህ ነው፤ በእነዚህ ሀያ ዓመታት ግዚ ኢትዮጵያ የሚባል ስም እንዳይነሳ ተደርጎ የነበረዉን አስከፊ “ሁኒታ” ለመለወጥ የሚደረገው ስብስብ ሁሉ በሊላ መሆን ግዲታ ነበር፤ የአፍሪቃ ቀንድ ስብስብ፤ የምስራቅ አፍሪቃ ጉባኢ፤ የትግራይ ነፃ አውጭ ፤ የኤርትራ ነፃ አውጭ ፤ የኦሮሞ ነፃ አውጭ፤ በመባባል ነው “ሁኒታው” የተፈጠረው፤ በኢትዮጵያ ስም መሰባሰብ ፍገጽሞ ክልክል ነበር። ዉጢቱም ኢትዮጵያ  የጎሳ ማሕደር ሆና አገርንቷ ቀርቶ የክልል መሪት መሆኗ ነው።፡ ይህንን ነው የጉግ ማንጉግ ፍልስፍና ያመጣብን፤ ዘርዕ ያዕቆብም ፈላስፋ ሊሆን አይችልም የተባለበትም ዋና ምክናያት ኢትዮጵያዉነትን ላለመቀበል ነው፤ ፕሮፊሰር ጌታቸው ኅይሊም ባለማወቅ ኢትዮጵያነትን ከሚያጠፋ ኅይል ጋር የተሰለፉ ይመስላል። በመጨረሻ ፕሮፊሰሩ በሰጡት አስተያየት ላይ አጠር ያለ ግንዛቤ ከተደረገ በኃሏ ወደሁለተኛው ዘርዕ ያዕቆብ ውይይት እንገባለን። ፕሮፊሰሩ ስለ ዘርዕ ያዕቆብ ፍልስፍና ሲፈላሰፉ እንዲዚህ ይላሉ፤

ሁለተኛ፥ ከሁሉም የሚገርመው .የኮከቦችን ቍጥር፥ ርቀታቸውን፥

ስለርቀታቸው ትናንሽ የሚመስሉን ትልቅነታቸውን ማን ያውቃል?.

ማለቱ ነው። ኮከቦች ትናንሽ የሚመስሉት በርቀታቸው ምክንያት

መሆኑን በቴለስኮፕ እንጂ በመፈላሰፍ የሚደረስበት አይደለም።

ይኸንንም የካቶሊኮቹ ተማሪ በነበረበት ጊዜ ከእነሱ አፍ አልሰማውም

ማለት ያዳግተኛል። ዋናው ቁም ነገር ግን ዘርአ ያዕቆብ የሚነግሩትን

             የሚሰማ ሰፊ ጆሮ፥ የሰማውን የሚመረም ትልቅ አእምሮ የነበረው ሰው

            መሆኑ ነው። የድርሰቱ ውበት ማንበብ የጀመረ ሳይጨርስ የማይለቀው

ነው። አማርኛዬ የግዕዙን ውበት እንዳስተጋባ ተስፋ አለኝ።

 

 

ዘርዕ ያዕቆብን “ጆሮና ተመራማሪ አእምሮ” አለው ብለው ከአመኑ “ቴለስኮፕና ካቶሊኮቹ”  ለምን ተጠቀሱ? ለመሆኑ ምን እንዳሉ አውቀዋል? ሲያውቁት የጻፉት “ንጥረ ነገር” ፈላስፋው “አሞ” ያለዉን ነው፤ “ጆሮ” አካል ፤ ደግሞ “አእምሮ”  ሕሊና መሆናቸዉን ነው። ይህንን አውቀው ቢሆን ኖሮ የጻፉት ይሕ ጸሐፊ በታላቅ ኩራት “ታላቁ ፈላስፋ ጌታቸው ኅይሌ እንዳሉት” እያልኩ ብጽፍ በጣም ደስ ይለኝ ነበር። ይህንን ስል አሁን ታላቅ አይደሉም ለማለት አይደለም፤ ታላቅ ምሑር መሆኖዎን አምናለሁ፤ ዘርዕ ያዕቆብን እንደገና በተረጋጋ መንፈስ ቢመረምሩት ሳያውቁ የጻፉትን አውቀው እንደሚጽፉት እርገጠኛ ነኝ፤ ጽሑፉዎን በችኮላ እንደጻፉት ያስታውቃል፤ ግዲለሽነት ይታይብታል፤ አረፈተ ነገሮች ተዝረክርከዋል፤ የቃላት አገባብ ችግር ጎልተው ይታያሉ፤ አግባብ ያልሆኑ ቃላት ተጠቅመዋል፤ ጽሑፉ ከእርስዎ ችሎታ ጋር አይመጣጠንም።

እርስዎ ግዕዙን በተለምዶ በደንብ ያዎቁቷል። የቋንቋ መምሕርም ስለሆኑ የግሱን ዕርባታ ጠንቅቀው ያዉቃሉ፤ ዘርዕ ያዕቆብ የግዕዝ መምሕር ስለሆነ ደግሞም ፍልስፍናዉን የጻፈው በግዕዝ ስለሆነና ትምሕርቱም በልምድ ሳይሆን በወንበር ስለሆነ ከሊላ አካል ሰምቶ ሳይሆን አውቆ የጻፈዉን ፍልስፍና በድጋሚ ቢመለከቱት ሊላ ድምዳሜ ላይ ይደርሳሉ ብዮ እገምታለሁ። በመጨረሻ የጻፉትን አርፍተ ነገር [“አማርኛዮ የግዕዙን ዉበት እንዳስታባ ተስፋ አለኝ”] ከአርስዎ ይልቅ ሊላ ጸሐፊ ቢጽፈው ጥሩ ነበር፤ ቀደም ብዮ እንድጻፍኩት “ትርጉሙ በሚገባ ተተርጉሟል” ብያለህ፤ እርስዎ ግን ሲሉት “ዕውነትም ፕሮፊሰሩ ዝና እና ውዳሴ ፈላጌ ናቸው” ብሎ እኔ የሰጠሁትን ትችት ሊደግፍ ይችላል፤ ምን አልባት ማሌቲ ነው። ይህንን ከአልኩ በኃሏ ወደ ሁለተኛው ዘርዕ ያዕቆብ ውይይት አመራለሁ።  

 

  1. የተጻፈ ለተግሳጽና ለትምህርት ተጻፈ

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ሰኔ ቀን 2 2015 . ሊናሕ

ሊናሕ

 

ትእይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩክ ወድቀ ላእሌየ። ወኩሉ ዘተጽሕፈ ለተግሳጸ ዚአነ ተጽሕፈ ከመ በትእግስትነ ወበተወክሎ መጻሕፍት ንርከብ ተስፋነ”ሮሜ 15፡ 3

 

ይህችን ጦማር “የተጻፈ ለተግሳጽና ለትምህርት ተጻፈ” በምትለው ሐረግ ላይ እንድመሰረትታ ያደረገኝ ተጽፎ ከቆየው መጽሐፍ በመፍለቋ ነው። የፈለቀችበት መጽሐፍ ጨካኞች በዜጎቻቸው ላይ መከራ በሚያበዙበት ወቅት መንፈሳቸውን በጽናት በተስፋና በስነ ምግባር እንዲያጠነክሩ የሚያሳስብ ነው። “የተጻፈ ለተግሳጽና ለትምህርት ተጻፈ” የምትለው ጥቅስ ለዚህች ጦማር ምክንያት የሆነችውን ጥንታዊት ክርታስ አጉልታ ስለምታሳይ ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወስድኳት።ይህችን ጥንታዊት ክርታስ ያቀበሉኝ ዶ ክተር ጌታቸው ኃይሌ ናቸው። “የታረዱት ነፍሳት ጩኸት” በሚል ርዕስ ከተባበሩት መንፈሳውያን ህብረት መግለጫ በሚመለከቱበት ወቅት እንዳጋጣሚ ከዚህ በታች የሰፈረችውን ክርታስ የያዘውን መጽሐፍ ይመለከቱ ስለነበር፤ ከተባባሩት መንፈሳውያን ህብረት መግለጫ ጋራ መመሳሰሏ ገርሟቸው ይህችን ክርታስ እንድመለከታት ከመጽሐፉ ቆንጥረው አቀበሉኝ።

ክርታሷን ሳነባት፤ በንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን የነበረውን ዘመን፤ አሁን ካለንበት ዘመን፤ መሪዎችን ከመሪዎች፤ አመራርን ካመራር፤ ጭፍራን ከጭፍራ፤ ካህናትን ከካህናት፤ ክስተቶችን ከክስተቶች ጋራ እያነጻጸረች የምታንጸባርቅ በመሆኗ እጅግ ተገረምኩ። ኢትዮጵያ እኔን ብቻ አልወለደችኝ፤ መገረሙ ለምን በኔ ብቻ ይወሰን፤ በዚህ ዘመን ያለ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ይመለክተታትና እንደኔ ይግረመው ብየ አሰብኩ። ክርታሷ በጥንታዊትነቷ የኢትዮጵያውን ንብረት በመሆኗ ፈቃድ መጠየቅ አስፈላጊ ባይሆንም፤ ከየትና እንዴት ከኔ እንደደረሰች አለመግለጽ የሚያስነቅፍ ነጠቃ ነው። በቅኔ ትምህርት ቤት የሚያስመሰግነው ነጠቃ፤ ባለ ቅኔው ካንደበቱ ሳያወጣው፤ በሚሰጠው ፍንጭ ምሥጢሩን በመቅደም መንጠቅ እንጅ፤  ካንደበቱ ካፈለቀው በኋላ የራስ አስመስሎ መናገር በጥብቅ ክልክል ነው። እንኳን ቅኔ ተራ ነገርም ቢሆን አፍላቂውንሳይናገሩ ከራስ የፈለቀ አድርጎ ማቅረብ የሰው ሀሳብ ዘራፊ፤ የሀሳብ ሌባ፤ መሳጢ፤ ጥራዝ ነጣቂ plagiarizerተብሎ ከሰውነት በታች ያወርዳል። በቅኔ ትምህርት ቤታችን ስርአት አሥር ሸክም እንጨት ከቆላ ማመላለስን ያስከትላል።

 

ሊናሕእጅግ በጣም የሚገርም አርዕስትና ጽሑፍ ነው፤ በመጀመሪያ ከሮሜ 15፡3 የተወሰደው ጥቅስ በግዕዝ “ወኩሉ ዘትጽሕፈ ለተግሳጸ ተጽሕፈ ከመ በተእግስትነ ወበተወክሎ መጻሕፍት ንረክብ ተስፋነ” የሚለው  ሐረግ በአማርኛ ግሱ ባለቤት፤ ተሳቤ እና ማሰሪያ ሆኖ ሲተረጎም ስሚት አይሰጥም። ለምሳሌ በቅዳሴ ግዜ “ለይኩን ለይኩን ቡሩከ ለይኩን” የሚለውን ቃለ ዉዳሴ ወደ አማርኛ እንደዚህ ብለው “ይሁን፤ይሁን፤ይመስገን ይሁን” ሲተረጉሙት  ፈጽሞ ስሜት አይስጥም። ትርጉሙ ቃል በቃል ሳይሆን በአማርኛ ሥዋስው ደንብ ባለቤቱና ማሰሪያ ግሱ ተቀነባብሮ መጻፍ ይኖርበታል፤ባለቤቱ ማለትም ምስጋና የቀረበው ለክርስቶስ ስለሆነ መባል የነበረበት “ስሙ ለዘለዓለም የተባረከ ይሁን” ነው ስሙ ውስጠ ታዋቄ ስለሆነ።ነገር ገን የግዕዝ ሥዋስዉ በሚገባ ስለአልዳበረ አረፍተ ነገሮች የሚጻፉት ጸሐፊው እንደመሰለው አድርጎ ነው፤ ከላይ የተሰጠው አርዕስት “የ” ሚለው ቅጽል ቢገደፍ የሚሆነው “ተጻፈ ለተግሳጽና ለትምህርት ተጻፈ” ስለሚሆን ስሚት አይሰጥም ምክናያቱም ግሱ ባለቤትም ማሰሪያም መሆን ስለማይችል፤ ነገር ግን “የ” የሚለው አመልካች ቅጽል ከገባ መጻፍ ያለብት “የተጻፈው ለተግሳጽና ለትምህርት ነው” ተብሎ ነው። የኛ ደብተራዎች  ግዕዙንም ሆነ አማርኛዉን በደንብ አድርገው ስለማያዉት የሚጽፉትም ሆነ የሚናገሩት እንደመሰላቸው ነው። አለማወቅ ደፋር ያደርጋል እንደሚባለው ሲያስተምሩም ሆነ ሲገሰጹ በድፍረት ነው። “ሰማይ ትወጣለህ፤ሲኦል ትወርዳለህ እያሉ ሕዝበ ክርስቲያኑን ሕሊናዉን ከማውገዝ በላይ የስውን ልጅ በሥነ ምግባር ኮትኩተው ፈሪሐ እግዚአብሒር እንዲኖረው አይደለም። ከላይ የተጠቀሰው አርዕስትና ጽሑፍ የተለመደው ውግዘት ነው። እንደዚህ አይነቱ አባባል ተግሳጽም ትምህርትም አይሆንም።

 

ይህ ከተባለ በኃላ ትልቁ ጥያቄ ለምንድነው ፕሮፊሰር ጌታቸው ኅይሌ አንድ ቁራጭ “ክርታስ” ለቀሲስ አስተርአየ ጽጌ እንድሚለከቷት የላኩት? ከርታሱ የተገኝበት መጽሐፍ ስምና ጸሐፊ ሊኖረው ይገባል፤ ለምንድነው የጸሐፊውና የተጻፈበት ዘመን ያልተገለጸው? በአርዕስቱ ላይ እንደተጻፈው ተግሳጹና ትምህርቱ አፂ ዘርዕ ያዕቆብ ስለ ሰራው አረማዊ ተግባር ነው? በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ ስለ ዘርዕ ያዕቆብ አረማዊነት የተጻፈ ነገር የለም፤ አሁን ግን አገኙት በተባለው “ክርታስ”     

አረምዊነቱን ለተግሳጽና ለትምህርት ተብሎ የቀረበበት ለምን ይሆን? ለመሆኑ ፕሮፊሰሩም ሆኑ ቀሲስ አስተርአየ ስለ ዘርዕ

ያዕቆብ አስፈላጊዉን ጥናት በማድረግ ነው “አረማዊ ስርአቱን” የተረዳችሁት? ወይስ ደግሞ በተዋህዶ ከርስቲያን ስም  የተደራጁ የወያኔ ተለጣፊ “ተሐድስዎች” ነን በሚሉት ፕሮጋንዳ ተነሳስታችሁ ነው በዘርዕ ያዕቆብ  ላይ የዘመታችሁት? ምክናያቱ ግልጽ አይደለም። ሆኖም አንባቢ ይህንን እውነት ያልሆነ ክስ እንዲመለከተዉና የራሱን አስተያየት እንዲስጥበት ተላክ የትባለዉን “ክርታስ” ግዕዙንና ትርጉሙን በዋቢነት ከዚህ በታች ይቀርባሉ።

 

 

“ዶክተር ጌታቸው የላኩልኝ ግእዙ”

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

 

ወእምድኅረዝ በፈቃደ እግዚአብሔር ለአከት ኀበ [አቡነ ተክለ ሐዋርያት]ዣን ከለላ ብእሲተ ንጉሥነ ዘርአ ያዕቆብ እሙ ለበእደ ማርያም፤ ወትቤሎ ናዝዘኒ ኀጢአትየ በእንተ ክርስቶስ። ወአሜሃ ሖረ ኀበ ዴዴ ንጉሥ ወናዘዛ ላቲ በከመ ሕግ። ወእምድኅረ ናዘዛ ትቤሎ ንግሥት ለአቡነ ተክለ ሐዋርያት ባእ ኀበ ወልድየ ወባርኮ። ወበእደ ማርያም ለአከ ኀቤሁ ወይቤሎ ባርከኒአ ወናዝዘኒ በእንተ ፍቅረ ክርስቶስ ወበእንተ ፍቅረ ማርያም ወእምዝ ቦአ ኀበ ገላውድዮስ [የበእደ ማርያም ሌላው ስም መሆን አለበት] ወቤተ እንዘ ይምዕዶ ወይናዝዞ በነገረ መጻሕፍት ቅዱሳት።ወእምህየ አብእዎ ኀበ ቤተ ንጉሥ። ወተስእሎ ንጉሥነ ዘርአ ያዕቆብ ኵሎ ግብሮ ወአፍቀሮ ወአንበሮ ኀበ ዴዴሁ ኀበ ታቦተ ማርያም ድንግል። ወነበረ በህየ ፫ተ አውራኃ። ወበዕለተ በዐለ መስቀል ርእየ አቡነ ተክለ ሐዋርያት በዴዴ ንጉሥ እንዘ ይትዋነዩ ሐራ በአፍራስ እንዘ ይደራበዩ በአእባብ ወበአዕፅምት ወበዘንግ እንዘ ይመውቱ ብዝዙኃን ነፍሳት። ወአንከረ ወይቤ ግዕዘ አረሚኑ ዝንቱ። ወሐዘነ ጥቀ ወይቤ ለምንት እነብር በከ ወኢይጌሥጽ ወኢይሜህር ሕገ። ወእመሂ አበዩኒ ይቅትሉኒ። ወነገሮሙ ለብዙኃን ካህናት ወመነኮሳት 3ይቤሎሙ ለምንት ኢንጌሥጽ ንጉሠ በዘኢኮነ ሕገ። ወይቤልዎን ንሕነሰ ንፈርህ፤ አንተ በል። ወበዕለተ በዐለ መስቀል ርእየ አቡነ ተክለ ሐዋርያት በዴዴ ንጉሥ እንዘ ይትዋነዩ ሐራ በአፍራስ እንዘ ይደራበዩ በአእባብ ወበአዕፅምት ወበዘንግ እንዘ ይመውቱ ብዝዙኃን ነፍሳት። ወአንከረ ወይቤ ግዕዘ አረሚኑ ዝንቱ። ወሐዘነ ጥቀ ወይቤ ለምንት እነብር በከ ወኢይጌሥጽ ወኢይሜህር ሕገ። ወእመሂ አበዩኒ ይቅትሉኒ።ወእምዝ ነበረ እንዘ የሐዝን ሠሉሰ ዕለተ። ወአመ ፳ወ፩ለመስከረም ለአከ ኀበ ንጉሥ ወይቤ ተመጠወኒአ። ብየ ነገር (=ጉዳይ) ኀቤከ። ወይቤሎ ንጉሥ ኢይትከሀለኒ ዮም፤ ወለአከ ኀቤሁ ፩ደ እምሊቀ ደብተራ ዘስሙ ገብረ ኢየሱስ ይንግሮ ሎቱ ነገሮ። ወነገሮ አቡነ (ለውእቱ ደብተራ) ኵሎ ዘይኄሊ (በእንተ) ሞተ ሰብእኒ በከንቱ ወበእንተ ማእሰርት ወዝብጠተ ኵነኔ ዘኢይከውን ዘይትገበር። ወለአከ አቡነ ብዙኀ ነገረ። ወተቃጸቦ ውእቱ ደብተራ ለአቡነ በልሳኑ (= ምላሱን አወጣበት) ወይቤሎ አብነ ነቢየ አምላክ አንተሂ ኢታመስጥ እምውእቱ መቅሠፍት። ወከማሁ ሞተ ድኅረ በእኩይ ኵነኔ ጽዑር። ወአሜሃ ቦአ (ውእቱ ደብተራ) በመዐት ኀበ ንጉሥ ወአስተዋደዮ ለአቡነ ወይቤ ይጼደቅ (= ይመጻደቃል) ዝመነኮስ ወይዛለፈከ። ወይፀርፍ ብዙኀ ላዕሌከ። ወበእንተዝ ተምዐ ንጉሥ ጥቀ፤ ወአዘዘ ያምጽእዎ ፍጡነ። ወሶቤሃ አብእዎ በጕጕዐ፣ ወይቤሎ ንጉሥ አማንኑ ዘለፍከኒ። መነ ርኢከ እንዘ እቀትል ዘእንበለ ፍትሕ። ወመነ አእመርከ እንዘ እኴንን ወእዘብጥ እንበለ ሕግ፤ ወለምንት ከመዝ ትዘልፈኒ እንዘ መሲሕ አነ። ይቤ አቡነ እንዘ እቀውም ቅድመ ንጉሥ ወረደ ላዕሌየ ኀይል እምአርያሙ ለአምላኪየ፤ ወሰማዕኩ ቃለ ዘይብለኒ ጽናዕ ፍቁርየ። ወእምዝ ተዋሥአ አቡነ ምስለ ንጉሥ ብዙኀ ነገረ በእንተ አንስት (“ማእሰርትሳይሆን አይቀርም) ወበእንተ ኵነኔ ወዝብጠት ብዙኀ ወበእንተ ኵሉ ዘኢይከውን ገቢረ። ወበእንተ ድፍረተ ተዋሥኦቱ ተምዐ ንጉሥ ዘርአ ያዕቆብ ወአዘዘ ይዝብጥዎ አፉሁ ወአእናፊሁ። ወዘበጥዎ ብዙኀ። ወውሕዘ ደም እምአንፉ ወአፉሁ። ወአቡነሂ ተዋሥኦ ወኢፈርሀ ምንተኒ ዝብጠተ። ወነዝሀ ደሞ ውስተ ምድር በቅድመ ንጉሥ፤ ወአጥመቀ በደሙ ሥልሰ ሥዕለ ማርያም ድንግል ምስለ ፍቁር ወልዳ ዘኮነ ይፀውራ በእንግድዐሁ። ወንጉሥኒ ወሰከ መዐተ ሶበ ርእየ ዘንተ። ወዳግመ ዘበጥዎ ብዙኀ። ወአዘዘ ይዕቀብዎ ሐራ ጽኑዓን፤ ወነበረ አቡነ በሕማም። ወካዕበ በኅዳጥ ዘመን ጸውዖ ንጉሥ። ወአሜሃኒ ጸንዐ አቡነ ወተዋሥኦ ለንጉሥ። ወዘበጥዎ ዳግመ በአብትር። ወአዘዘ ንጉሥ ያንብርዎ ውስተ ምንድቅ ምስለ ሐራ።

 

 

“የግእዙ ትርጉም”

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

 

የንጉሣችን ዘርአ ያዕቆብ ባለቤት፤ የብእደ ማርያም እናት ዣን ከለላ ይባሉ የነበሩት ንግሥት ከዕለታት አንድ ቀን፤ ኃጢአታቸውን ተናዘው ንስሀ ለመግባት ፈለጉና፤ በዘመናቸው የነበሩትን መንፈሳዊ አባት አባ ተክለ ሐዋርያትን ወደ ቤተ መንግሥት አስጠሯቸው። መንፈሳዊው አባትም ጥሪውን ተቀብለው ወደ ቤተ መንግሥት ሄዱ። ንግሥቲቱን መክረው አስተምረው ተገቢውን ንስሀ ሰጧቸው። ንግሥቲቱም በእደ ማርያም ይባል የነበረውን ልጃቸውንም እንዲመክሩላቸው እንዲያስተምሩላቸው መንፈሳዊውን አባት ጠየቌቸው። በእደ ማርያምም በእናቱ ምክር ተስማምቶ ከመንፈሳዊው አባት ቡራኬ ለመቀበል ፈቀደ። መንፈሳዊው አባትም መጻሕፍትን እየጠቀሱ በእደ ማርያምን መክረው አጽናናተው ባረኩት። ከዚያ በኋላ መንፈሳዊውን አባት ወደ ንጉሡ አቀረቧቸውና ከንጉሥ ዘርአ ያዕቆ ጋራ ተገናኙ። ንጉሡም የመንፈሳዊውን አባት ብቃትና ችሎታ ለማወቅ ፈልገው፤ ጥያቄዎችን አቅርበውላቸው በሰጧቸው መልስ ብቃታቸውን ከተረዱ በኋላ፤ ከቤተ መንግሥቱ በር አጠገብ በነበረችው በእመቤታችን ስም በተሰየመችው ቤተ ጸሎት (ኒቆታ) ውስጥ እንዲቀመጡ ፈቀዱላቸው። መንፈሳዊው አባትም በቤተ መንግሥቱ ጸሎት ቤት ለሶስት ወራት ቆዩ። በቤተ መንግሥቱ ፊት ለፊት በነበረው ሜዳ ላይ፤ የመስቀል በዓል በየዓመቱ ሲከበር በሚደረገው ስርአት የንጉሡ ጭፍሮች በፈረስ ግልቢያ በመወዳደር እስኪ ጎዳዱና እስኪ ገዳደሉ ድረስ እርስ በርሳቸው በዱላ ባጥንት በዘንግ ሲደባደቡ ሲቀጣቀጡ መንፈሳዊው አባት አዩ መንፈሳዊው አባትም፤ ንጉሡ ይህን አረማዊ ባህል ከማረም ይልቅ እንዲካሄድ በመፍቀዳቸው በጣም አዘኑ። መንፈሳዊው አባትምይህን ያረመኔ ተግባር እያየሁ በቤተ መንግስት ውስጥ በምቾት በመቀመጥ ጊዜየን በከንቱ ማባከን ነው። ንጉሡን መክሬ አስተምሬ ይህንን አረማዊ ልማድ እንዲያቆሙ መድረግ አለብኝብለው ወሰኑ። በመጀመሪያ በማስቆሙ እንቅስቃሴ ላይ ካህናቱ እንዲተባበሯቸው ጠየቁ። ካህናቱ ግን ከፈለጉ እራሰዎ ያድርጉት እንጅ እኛ ንጉሡን እንፈራለን ብለው ሊተባበሯቸው አልፈለጉም። መንፈሳዊው አባትም፤ ካህናቱባይተባበሩኝም፤ ንጉሡ ምክሬንና ተግሳጼን ባይቀበሉም፤ ሊገድሉኝ ቢፈልጉም ይግደሉኝ እንጅ፤ ይህን አረማዊ ተግባር እያየሁ ዝም ብየ ዘመነኔን በከንቱ አላሳልፈውምብለው ወሰኑ። ወደ ንጉሡ ከመቅረባቸው በፊት ለሶስት ቀናት ከአምላካቸው ኃይልና ድፍረት እንዲያገኙ ጾሙ ጸለዩ ። ከሶስት ቀናት ጾምና ጸሎት በኋላ ለግርማዊነተዎ የማቀርበው ትልቅ ጉዳይ አለኝና ይፍቀዱልኝ ብለው መስከረም 21 ቀን ወደ ንጉሡ ላኩ። ንጉሡም ታማኝ አገልጋዮቻቸው ከነበሩት ከደብተሮች አለቆች አንዱ ገብረ ኢየሱስ በሚባለው በኩልለዛሬ አይመቸኝምብለው መለሱላቸው። መንፈሳዊው አባትም ለንጕሡ ማቅረብ ያሰቡትን ለደብተራ ገብረ ኢየሱስ አካፈሉት። ማቅረብ ያሰቡትም፤በቤተ መንግስት አደባባይ ላይ ሰዎች እርስ በርሳቸው እየተደባደቡ እስከ መጋደል መድረሳቸው ለሰው ልጅ ክብር ተስማሚ አይደለምየሚል ሲሆን፤ በቤተ መንግሥት በቆዩበት ወቅት የታዘቧቸውን ሌሎችንም ስህተቶችመታረም ይገባቸዋልብለው ለደፍተራ ገብረ ኢየሱስ አካፈሉት። ደብተራ ገብረ ኢየሱስ መንፈሳዊው አባት ለንጉሡ እንዲያደርሱላቸው የነገሩትን መልእክት ለንጉሡ ሊያደርስ ይቅርና፤ ራሳቸው ይህን ድፍረት የተሞላ አቀራረብ ለንጉሡ ለማቅረብ በማሰባቸው እጅግ ተገረመ።ደፍተራ ገብረ ኢየሱስነቢየ አምላክ ሆይንጉሡ ሠራዊቱ የሚያደርገውን አረማዊ ባህል እንዲያስቆሙ ሊያስደርጉ ይቅርና፤ እርሰዎንስ ከጭፍራው ተቀላቅለው ይደባደቡ ብለው ግርማዊነታቸው ቢያዝዘዎ ምን ሊሉ ነውብሎ መለሰላቸው። ከዚያ በኌላ ደፍተራውይዘልፍዎታል፤ ይንቅዎታልእያለ መንፈሳዊውን አባት ከንጉሡ ጋራ የሚያራርቅና የሚያጋጭ፤ የሚያስቆጣ ነገር እየጨመረ ለጉሡ ነገራቸው ጉሡም ደፍተራው በነገራቸው የተጋነነ ነገር በመንፈሳዊ አባት ላይ ቁጣቸው ነደደ።አፍቅሬና አክብሬ በቤተ መንግሥቴ ባስቀምጣቸው እንዴት ይህን ያህል ሊንቁኝና ሊደፍሩኝ በቁ በፍጥነት አምጧቸውብለው ንጉሡ ወታደሮችን አዘዙ። ወታደሮችም መንፈሳዊውን አባት እያዳፉ ወደ ንጉሡ አቀረቧቸው። ንጉሡምግርማዊነታችንን እየዘለፉ ለደፍተራው የነገሩት እውነት ነውከህግ ውጭ ማንን ስንገርፍና ስንገድል አዩ እንዴት ስማችንን ያጠፋሉ ብለው በመንፈሳዊው አባት ላይ የቁጣ ቃል አወረዱባቸው። መንፈሳዊ አባትም የንጉሡን ቁጣና ግልምጫ አልተቀበሉም። ይልቁንምንጉሥ ሆይ በቁጣ የተናገሩትን ልሰማዎና ልቀበለዎ ይቅርና፤ የቁጣዎ ቃል ካንደበተዎ በሚጎርፍበት ቅጽበት፤ ከርሰዎ ቁጣ የበለጠ ኃይል ያለውወዳጄ ጽናየሚል ድምጽ ከአምላኬ ዘንድ ሰማሁብለው በቁጣና በድፍረት ለንጉሡ መለሱላቸው። ቀጠሉናባካባቢዎ የሚፈጸሙት የፍርድ መዛባት፤ ዝሙትና ግርፊያ መቆም ይኖርባቸዋልብለው በድፍረት ተናገሩ።ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብም መንፈሳዊው አባት በድፍረት በመናገራቸው አፋቸውንና አፍንጫውን እንዲደበደቡ አዘዙ። ካፍንጫቸውና ካፋቸው ደም ጎረፈ። ይህ የሚደርስባቸው ሥቃይ ሳይገታቸው መንፈሳዊው አባት ለንጉሡ ሊነገር የሚገባውን ተግሳጽ መናገራቸውን ቀጠሉ። በደረታቸው የነበረችውን የእመቤታችንን ስእለ አድህኖ እንደ ውሀ ከሚፈሰው ደማቸው በንጉሡ ፊት ሶስት ጊዜ ቀቡ። ንጉሡም በደማቸው ስእለ አድህኖውን ሲቀቡ ባዩ ጊዜ ቁጣቸው እጅግ ነደደ። ድብደባው እንዲቀጥል ትእዛዛ ሰጡ። ወደ ጽኑ እስር ቤትም እንዲወሰዱ ወታደሮችን አዘዙ። ከጥቂት ዓመታት በኋላ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ መንፈሳዊውን አባት ከእስር ቤት አስመጧቸው። መንፈሳዊው አባትም ከቀድሞው እጅግ በጠነከረ መንፈስ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብን ገሰጿቸው። ንጉሥ ዘርዓ ያእቆብም በመንፈሳዊው አባት ላይ ቁጣቸው የበለጠ ነደደ። አስደበደቧቸው፤ ወደ ጽኑ እስራትም እንዲመለሱ አዘዙ። የመንፈሳዊ አባት መንፈሳዊ ኃይላቸው እየጋለ ቢሄድም፤ ከበትሩና ከእንግልቱ ጽናት የተነሳ ሰውነታቸው ደከመ

 

 

ከላይ የተጻፈው የግዕዝና የአማርኛ ትርጉም ስሚት የማይሰጥ ዝርክርክ የአለ ኃሳብ ነው።፡ ሥነ ጽሑፉ የሥዋሱን ደንብ ስለአልተከተለ ምን ለማለት እንደተባለ ለማወቅ ያስቸግራል፤ ለምሳሌ በግዕዙ ላይ “ወ” የሚለው አገኛኝ መስተዋድድና መስተፃምር በቁጥር አምሳ ይደርሳሉ። መስተዋድድ በአራት ነጥብም ሆነ በድርዝ ሰረዝ አይገታም፤ ምክናያቱም ነጠላ ነገሮችን ስለሚያይዝ ። ለምሳሌ “ፀሐየ ወወርኃ ወክዋክብት ወኩሎሙ ሥልጣናተ ሰማይ እለ ይትመየጡ የዓርቡ በመካኒሆሙ ወበአዝማኒሆሙ ወበዓላቲሆሙ ወበአዉርኂሆሙ” የሚለው ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተወሰደው ግዕዝ “ወ” የሚለዉን መስተዋድድ በሚገባ አረፈተ ነገሩን አያይዟል፤ እዚህ ላይ አንባቤ በትኩረት ማስተዋል ያለበት “ወ” የሚለው አገናኝ መስተዋድድ በምልክት አልታገደም። ቢታገድ ኖሮ ንባቡ ስሚት አይስጥም ነበር፤ ፕሮፊሰር ጌታቸው ኅይሌ ለቀሲስ አስተርአየ  ጽጌ ያቀበሉት “የዘርዕ ያዕቅብ አረማዊነት የተጻፈበት ግዕዝ ፈሞ ስሚት የማይሰጥ ዝርክርክ ያለ አረፈተ ነገር ነው። ማን እንደጻፈው ለግዜው ባይታወቅምም የት እንደተጻፈ ለማወቅ አስቸጋሪ አይሆንም፤ ጽሑፉ “ሃምስ” ስለሚበዛበት የግዕዝ መምህራን ዘይቤው ከየትኛው ክፍለ አገር እንደሆነ ሊነግሩን ስለሚችሉ ጉዳዩን ለቧለሟዎቹ እተዋለሁ። ይህን ከተባለ በኋላ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ስለሰጡት “ሐተታ” እና “ነጸብራቅ” ትንሽ ዉይይት ማድረግ አስፈላጊ ነው፤ ለውይይቱ እንዲረዳን “ሐተታውን” እና “ነጸብራቁን” ከዚህ በታች ሙሉ በሙሉ ለአንባቢ ይቀርባሉ፤

 

 

 

ሐተታ

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

 

አንባብያን ሆይ !ይህች ጥንታዊት ክርታስ የያዘችው የንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብን አረማዊ ስርአት ሲሆን፤ የአባ ወልደ ሐዋርያትን መንፈሳዊ ጽናት፤ የደፍተራ ገብረ ኢየሱስን መሰርይነት፤ የካህናቱን ምንደኛነት እና ሠራዊቱን እርስ በርሱ ያጋድል የነበረውን የንጉሥ ዘርአ ያዕቆብን ጨካኝነት አጉልታ ታሳያለች።አዕይነተ እግዚአብሔርነን የሚሉ፤ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንእየተባሉ የሚሰብኩ የሚቀድሱ የሚዘምሩ በዚያ ዘመን የነበሩ ካህናት የሚደረገውን ሁሉ ኃጢአት አስቀድመው በማየት፤ ተባብረው መገሰጽና ማስቆም ነበረባቸው። በእግዚአብሔር አዕይንነታቸው ከሁሉ አስቀድመው የሚደረገውን ግፍ ማየታቸው ይቅርና፤ ያዩት አባት ለማስቆም ተባበሩኝ ቢሏቸው ፈርተው አንተባበርም አሉ። ግን ዝማሬውን ቅዳሴውን ስብከቱን በየደብራቸው ያካሄዳሉ እርስ በርሱ የሚያጋድለው የንጉሡ አረመናዊው ተግባርም ጎን ለጎን ይካሄዳል። ከህዝቡ የተሻሉ አዋቂዎች ቅዱሳኖች መስለው እንደ ደፍተራ ገብረ ኢየሱስ የመሰሉ ሰራዊቱንና ህዝቡን የሚያደነዝዝ፤ ፉከራ መሳይ ስብከታቸውን አላቋረጡም። አረማዊ የሆነውን ባህል እንዲያቆሙ ንጉሡን ከመገሰጽ ይልቅ፤ ህዝቡን ሠራዊቱን ንስሀ ግቡ እያሉ ማደንቆራቸው ሲቀጥሉ ህሊናቸው አልወቀሳቸውም። መንፈሳዊው አባትምካህናቱ ባይተባበሩኝም በነ ደፍተራ ገብረ ኢየሱስ ነገር አቀባባይነት የመጣውን መከራ እቀበላለሁ እንጅ ይህን ያረመኔ ተግባር እያየሁና እየሰማሁ በቤተ መንግስት በምቾት በመቀመጥ ጊዜየን በከንቱ አላባክንም። ንጉሱን መክሬ አስተምሬ ማስቆም አለብኝብለው ወሰኑ። በመጀመሪያ በማስቆሙ እንቅስቃሴ ላይ ካህናቱ እንዲተባበሯቸው ሞከሩ።ወደ ንጉሡ ከመቅረባቸው በፊት ለሶስት ቀናት ከአምላካቸው ኃይልና ድፍረት እንዲያገኙ ጾሙ ጸለዩ ይህ ሁሉ ለደብተራ ገብረ ኢየሱስ ሰርግና ምላሽ ነበር። ደፍተራ ገብረ ኢየሱስ ከመንፈሳዊ አባት የሰማውን እየገለበጠ ለንጉሡ በማቅረብ ለንጉሡ ተወዳጅነቱን ታማኝነቱን ማረጋገጫ አድርጎ ተጠቀመበት። መንፈሳዊውን አባት ለራሱ የባለሟልነት ማዳበሪያ በማድረግ ለመከራና ሥቃይ ዳረጋቸው። ደፍተራ ገብረ ኢየሱስም፤ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብም፤ ካህናቱም እርስ በርሱ ይጋደል የነበረው ህዝብም በዚህች ዓለም ላይ የሉም። መከራና ሥቃይ የደረሰባቸው አባ ወልደ ሐዋርያትም በዚህች ዓለም የሉም። ለሁሉም ለተሰቃዩ ለአባ ወልደ ሐዋርያትትም፤ አባ ወልደ ሐዋርያትን ላሰቃዩ ለነ ዘርዓ ያዕቆብም የነበረቻቸው የቆይታ ጊዜያቸው ትንሽ ነበረች። ሁሉም በምታልፈዋ በጥቂት ዘመን ቆይታቸው ሊሚያገኙት ቅንጦትና ድሎታቸው ሲሉ በሰማይና በምድር ለዘላለም ሲያስወቅስና ሲያስከስስ የሚኖር ሥራ ሰርተው አለፉ። አባ ወልደ ሐዋርያትበተፈጥሮ ሞት የሚመጣውን የአካል መፍረስ ተቀምጦ መጠበቅ ዘመንን በከንቱ ማባከን አሉበማይቀረው ተፈጥሯው ሞት ሞተው አካላቸው በመቃብር ከመፍረሱ በፊት፤ በንጉሡ ትእዛዝ በወታደሮች እጅ አካላቸው መፍረሱን መረጡ። የንጕሥ ዘርዓ ያዕቆብ ሠራዊቶች በተፈጥሮ ሞት መፍረሱ የማይቀረውን የአባ ሐዋርያትን ሥጋ ብትር ቀጥቅጠው በማፍረስ፤ ወደ መቃብር ትልነት ራሳቸውን ለወጡ። አሁን ሁሉም በዚህ ዓለም አጭር ቆይታቸው የሰሩትን ተግባር ተሸክመው በሰማያዊ አምላክ ፊት በዘላለማው ፍርድ ላይ ናቸው። በምድርም በየዘመኑ በሚነሳው ትውልድ እየተወቀሱና እየተከሰሱ ናቸው። አባ ወልደ ሐዋርያት ግን ባጭር ዘመን ቆይታቸው፤ ላጭር ጊዜ በደረሰችባቸው መከራና ስቃይ፤ በዘላለማዊ አምላክ ፊት ዘላለማዊውን ጸጋና ክብር ተቀዳጁበት። በምድርም በየዘመኑ በሚነሳው ትውልድ በምሳሌነታቸው እየተወደሱ እየተሞገሱ ይኖራሉ። አሁንም ለኛ ሕያው መምህራችን ናቸው።

 

“ነጸብራቅ”

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

 

ዘርዓ ያዕቆብ በማይገሰሥ ንጉሣዊ ስልጣናቸው እየታገዙ፤ አረማዊ ስርአታቸውን በመጠቀም፤ በህዝብ ላይ የፈፈጸሙት በደል፤ ዛሬ ራሳቸውን ወደ ንጉሥነት የለወጡ ወያኔዎች በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጽሙትን እጅግ የከፋ በደል ያንጸባርቃል። ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ ሠራዊታቸውን እርስ በርሱ ያቀጣቅጡ፤ ያደባድቡና ያጋድሉ እንደነበረ። ራሳቸውን ወደ ሞናርኪነት የለወጡ ወያኔዎችም ከህዝቡ አብራክ የፈለቀውን ኢትዮጵያዊ እየመለመሉ እርስ በርሱ በሚያጋድል በቅኝ ግዛት መርኌቸው አሰልጥነው እርስ በርሱ እያጋደሉት ነው። ወያኔዎች ከሰራዊቱ አልፈው፤ ከንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብም በከፋና እጅግ በሰፋ አረማዊ ዘዴያቸው መላ ኢትዮጵያውያን በጎሳና በቋንቋ ከፋፍለው እርስ በርሱ እያደባደቡትና እያጋደሉ ናቸው። በቤተ ክርስቲያናችን ሳይቀር ተሀድሶና ማህበረ ቅዱሳን የሚባሉ ድርጅቶ ፈጥረው፤ በቀሩት አኀት አብያተ ክርስቲያናት ወጣቶች ላይ በማይታይ ድሮ ባልነበረ ስርአት በነገረ መለኮት እያስመሰሉ ወጣቶችን በመከፋፈል እርስ በርሳቸው እያደባደቧቸው ነው።  ከፕሮፌሰር አስራት ጀምሮ በቅርቡ ቀጥቅጠው የገደሉትን ወጣት ሳሙዔል አወቀን የመሳሰሉ እንደ አባ ወልደ ሐዋርያት መንፈሰ ጠንካሮች፤ እርስ በርስ አጋዳይ የሆነውን የወያኔን አረማዊ ልምድ ለማስቆም ተባበሩን ብለው ላካባቢያቸው ካህናት ድምጻቸውን አሰሙ። ካህናቱም ወያኔን እንፈራለን እናንተው ተወጡት ብለው ፊታቸውን ወደ ወያኔ አዞሩ።ይህን ያረመኔ ተግባር እያየሁ በቤተ መንግስት በምቾት በመቀመጥ ጊዜየን በከንቱ ከማባከን፤ የሚገጥመኝን መከራ መቀበሉን እመርጣለሁብሎ፤ እንደ ሳሙዔል የሚወስን አንድ የሲኖዶስ አባል ወይም አባ የሚባል መነኩሴ ጠፋ። ወያኔ ከሚፈጽመው ተግባር እንዲገታ በማስቆሙ ከመተባበር ይልቅ በተቃራኒው ደፍተራ ገብረ ኢየሱስን ከመሳሰሉት ጋራ በመተባበር የወያኔን አረማዊ ተግባር የሚደግፉ ቆሞሶች ቁጥራቸው በዛ። ወደ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ ከመቅረባቸው በፊት ከአምላካቸው ኃይልና ድፍረት እንዲያገኙ ለሶስት ቀናት እንደ ጾሙት እንደ አባ ወልደ ሐዋርያት ወደ አምላክ ከመቅረብ ይልቅ፤ በወያኔ ዘመን ያሉ ሰባቂወች ጳጳሳት ቀሳውስትና መነኩሴዎች ብርታትና ድፍረት ከወያኔ የሚፈልጉ ሆኑ። ወያኔን ከፋፍለህ አታግድል ማለት ፖለቲካ መግባት ነው ብለው ዘበቱ። እንደነሱ አባባል የወኔ መመሪያና ተግባር የፖለቲካ ነክኪ የሌለው፤ መገሰጽ የሌለበት፤ ነገረ መለኮት የሚቀበለው ለሰው ልጅ ተስማሚ ነው ማለታቸው ነው። ደፍተራ ገብረ ዮሐንስ ከአባ ወልደ ሐዋርያት የሰማውን መልካም ምክር እየጠመዘዘ ለራሱ ባለሟልነት ማረጋገጫ እያደረገ ለንጉሡ እንዳቀረበው፤ የዘመናችን ሰባቂዎችም ወያኔን ሊመክሩና ሊገስጹ ይቅርና፤ ለወያኔዎችንም ያልተባለውን ሁሉ ወሬ በማቀበል ወያኔዎችን የከፉ አውሬዎች እየደረጓቸው ነው። በህዝቡ መካከል የሚከሰተውን ሁሉ ወደ ራሳቸው ጥቅምና ዝና እየቀየሩ ህዝቡን ይበዘብዛሉ፤ ከወያኔ ጋራ ያላቸውን ባለሟልነትና ታማኝነት ከፍ ያደርጋሉ። ለወያኔዎች ጨማምረው ወሬ እያቀበሉ እንደ አባ ወልደ ሐዋርያት ያሉትን ያስደበድባሉ፤ ያሳስራሉ፤ ያስገድላሉ። በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን የነበሩት ካህናት፤ ክርስቶስን በመከተል ሐዋርያት የሰሩትን፤ እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፤ እነ ቅዱስ ቄርሎስ ያደረጉትን ለመስራት ከአባ ወልደ ሐዋርያ ጋራ መተባበር ከዘርዓ ያዕቆብ ጋራ ያጋጨናል እያሉ ከአባ ወልደ ሐዋርያት እንደ ሸሹ። አባ ወልደ ሐዋርያትን ብቻቸውን እንዳቆሟቸውም፤ የዘመናችን ቆሞሳት ካህናት ሰባቂዎችም ጠንክረው ለመቆም የሚሞክሩትን አንዳንድ አባቶች ብቻቸውን አቆሟቸው። ህዝቡ የጠንካሮች ካህናትን አቋም አይቶ በምሳሌ በመከተል በነሱ ላይ እንዳይነሳባቸው መናፍቅ ናቸው፤ ማርያምን ክደዋል ብለው አሶሩባቸው። ፖለቲካ ውስጥ መግባት ነው እያሉ፦ አትግደሉ፤ ገዳም አትድፈሩ፤ አትሰሩ፤ አታሳዱ ከሚባልበት አውደ ምህረት ሁሉ ሸሹ። ወደ ማያስከስሰው ዳቦ ድግስ ወደ ሚያበላውና ሳንቲም ለማስለቀም ወደ ሚመቼው ወደ ሽብሸባው ዝማሬውና ቅዳሴውና ስብቀቱ ፊታቸውን አዞሩ። እኩይ ፍልስጣ እንደሚባለው ሰይጣን በነገረ መለኮት እየተቃኙ ለህዝብ ከሚቀርበው ትምህርት፤ ቃላት እየመዘዙ ወደራሳቸው ስሜት ጠምዝዘው ለህዝብ በማቅረብ እጅግ የፈጠኑ ሆኑ። በዚህች ነጸብራቅወደ ሽብሸባ ዝማሬና ቅዳሴ ፊታቸውን አዞሩብየ የተናገርኩትን ወደራሳቸው ፍልስጣዊ ሀሳብ ጠምዝዘው፤ ይኸዋ ያባቶቻችን ስርአት ነቀፈላችሁ ብለው ለየዋሁ ህዝብ ማቅረባቸውን ስለማይተው፤ እኔ ይህን ያልኩበት ቅዳሴው የሚናገረውን በዜማ ሸፍነው መልእክቱን ማፈናቸውን ለመናገር መኑን ለመግለጽ እንጅ፤ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ሥርአት ለመንቀፍ እንዳልሆነ፤ የደፍተራ ገብረ ኢየሱስ ተማሪዎች ሀሳቤን ከመጠምዘዛቸው በፊት በዚሁ አጋጣሚ እንዲገቱ አሳስባቸዋለሁ። በክርስትና ታሪክ እንደ ሐዋርያት በዘመናቸው የነበሩትን አረማውያን፤ ሊቃውንት አበውም በዘመናቸው የነበሩትን ሰባዊ ክብርን የሚያዋርዱ እንደ አባ ወልደ ሀዋርያት ዘርዓ ያዕቆብን፤ አቡነ ጴጥሮስም ጣሊንን ሲገስጹ እንጅ፤ አሸበሸባችሁ ዘመራችሁ ቀደሳችሁ ድሀውን ህዝብ ንስሀ ግቡ አላችሁ በመባል የታሰረ የተገደለ የለም። እንዲያውም ዜጎች በፈጣሪያቸው እየተማረሩ እድላችን ነው እያሉ እንደ ወያኔ ያለውን እንዳይቋቋሙ ስለሚያፈዝላቸው ወያኔን የመሰሉ መሪወች ይህን መሳይ የካህናት አቌም ይፈልጉታል። ይደግፉታል እነ ማርክስን የፈጠራቸውም ገለልተኛ በመምሰል ከወያኔ አይነቶች ጋራ ሰምና ወርቅ ሆኖ የሚቀርበው የሰባኪዎች ስብከትስብቀት ነው። ስብከትና ስብቀት እርስ በርሳቸው እየተቃረኑ ሀሳብ የሚወራረሱ ቃላት ናቸው። ስብከት ማለት ህዝቡ በጎ ነገር እንዲያስብና እንዲያመነጭ በነገረ መለኮት አቅጣጫ ማሳየት ነው። ስብቀት ግን ህዝቡ እውነቱን እንዳያይ ይልቁንም እርስ በርሱ እንዲከፋፈል። እርስ በርስ መጠራጠርን መፍዘዝን መደንዘዝን እየተናገረ የህዝቡን መንፈስ እንደ ደፍተራ ገብረ ኢየሱስ በነገረ ሰይጣን መስበቅ ነው። ስብከት የህዝብን አዕምሮ እየናጠ እምነትን ተስፋን ጽናትን መዋደደድን መግባባትን መደጋገፍን መተባበርን እንዲያመነጭ ማድረግ ነው። ስብቀት ግን ደፍተራ ገብረ ኢየሱስ በዘርዓ ያዕቆ ብና በአባ ወልደ ሐዋርያት ላይ እንዳደረገው፤ ህዝቡን እንደወተት እየገፋ እርስ በርስ መጠራጠርን መራራቅን መጣላትን እንዲያመነጭ ማድረግ ነው። ሁሉም በምታልፈዋ ለጥቂት ዘመን ቆይታቸውና ድሎታቸው ሲሉ በሰማይና በምድር ለዘላለም ሲያስወቅስና ሲያስከስስ የሚኖር ሥራ ሰርተው እንዳለፉ፤ እኛም በትንሿ የቆይታ ዘመናችን በሰማይና በምድር የሚያስወቅስ የሚያስከስስ ህዝብ የሚጎዳ ሥራ እንዳንፈጽምባት እንጠንቀቅ። በተፈጥሮ ሞት የሚመጣውን መፍረስ ተቀምጦ መጠበቅ ዘመንን በከንቱ ማባከን ነው እንዳሉት እንደ አባ ወልደ ሐዋርያት። በህዝቡ ላይ የሚደርሰውን ግፍና መከራ ፖለቲካ ነውና፤ አላይም አልሰማም ምንአገባኝ በማለት የየደብሮቻችን ዘበኞች በመሆን ዘመናችንን በከንቱ እንዳናሳልፈው እንጠንቀቅ። ተወዳጅነትን ታማኝነትን ለማትረፍ ከወያኔዎች ጋራ የቆሙትን ካህናት ከመምሰል ይልቅ፤ በወታደሮች እጅ አካላቸው መፍረሱን የመረጡትን አባ ወልደ ሐዋርያትን እንምሰል። ሁሉም በዚህ ዓለም አጭር ቆይታቸው የሰሩትን ተግባር ተሸክመው በሰማያዊ አምላክ ፊት በዘላለማው ፍርድ ላይ መሆናቸውን አንርሳ። በምድርም በየዘመኑ በሚነሳው ትውልድ እየተወቀሱና እየተከሰሱ መኖራቸውንም አንዘንጋ። አባ ወልደ ሐዋርያት ግን ባጭር ዘመን ቆይታቸው፤ ላጭር ጊዜ በደረሰችባቸው መከራና ስቃይ፤ በዘላለማዊ አምላክ ፊት ዘላለማዊውን ጸጋና ክብር መቀዳጀታቸው አይጠረጠርም። በምድርም በየዘመኑ በሚነሳው ትውልድ በምሳሌነታቸው እየተወደሱ እየተሞገሱ ይኖራሉ። አሁንም ለኛ ሕያው መምህራችን ናቸው።የተጻፈ ለተግሳጽና ለትምህርት ተጻፈእንዳለው ቅዱስ ጳውሎስ ይህች ጥንታዊ ክርታስ በዚህ ዘመን ላለን ኢትዮጵያውያን ተግሳጽና ትምህርት መሆኗን እንረዳ ዘንድ እግዚአብሔር ዓይነ ልቡናችንን ይክፈትልን።

 

 

ከላይ የተጠሰዉን “ሐተታና ነጸብራቅ” ጸሐፊው ከተላከላቸው ክርታስ በላይ ስለ ዘርዕ ያዕቅብ  ታሪክ የሚያቁት ነገር ከአለ ማስረዳትና ማስተማር ተገቢ ነው የሚል እምነት አለኝ፤ ነገር ግን መምህሩ የሰጡት “ሐተታና ነጸብራቅ” መሰረቱ ፕሮፊሰሩ በአቀበሏቸው ተረት ከሆነ ሃላፊነት የጎደለው ሥራ ስለሆነ ያስጠይቃችዋል። የመምህሩ የግዕዝ ችሎታ እንደ ፕሮፊሰሩ በመስማትና በልማድ ሳይሆን በወንበር ስለሆነ አንድ ዋሾ ደብተራ የጻፈዉን ተረት መሰረተ ቢስ መሆኑን ማወቅ ነበረባቸው፤ ለዚህም ምንም አይነት ምክናያት መስጠት አይችሉም ፤ ለአደረጉት ስሕተት ይቅርታ ጠይቀው  ራሳቸው እንዳሉት “በቅኔ ትምህርት ቤት”ሥራዓት ደንብ መሰረት “የአስር እንጨት ሽክም ከቆላ” የመሽከም ግዴታ አለባቸው። ምክናያቱን በአጭሩ ማስረዳት አስፈላጌ ነው፤ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በመግቤያቸው ላይ እንደሚሉት ከሆነ ለአርዕስታቸው የተጠቀሙት ጥቅስ የወሰዱት ከቅዱስ ጳውሎስ መልክት ላይ ነው ይላሉ፤ ቀጥሎም ከፕሮፊሰሩ የተሰጣቸው ክርታስ የመነጨችው ጥንታዊትና ከቆየው መጽሐፍ ላይ በማለት ለአንባብያን ስለ ዘርዕ ያዕቅብ አረማዊነት ሐተታቸዉን ይጀምራሉ፤ ነገር ግን ጥንታዊ የተባለው መጽሐፍ ምን ግዜ እንደተጻፈ ደግሞም ማን እንደጻፈው አያመለክቱም። “በነጸብራቅ” ላይ የአንጸባረቀላቸው ዘርዕ ያዕቆብ “በማይገስጽ ንጉሣዊ ስልጣኑ የአረማዊነት ሥራዓቱን በመጠቀም በሕዝቡ ላይ የፈጸመው በደል ዛሬ ራሳቸዉን ወደንጉሥነት የለወጡ ወያኔዎች በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚፈጽሙትን እጅግ የከፋ በደል ያንጽባርቃል።” እንግዲህ አንባቢ በትኩረት መመልከት ያለበት ዛሬ ወያኔ የሚፈጽመው በደል ከጥንት የአለ ስለሆነ አዲስ ነገር የለም ለማለት ነው፤ ግዕዙም ትርጉሙም የሚለው ይህንን ነው። በምን ዓይነት መለኪያ ወይስ እይታ ነው ይህ “ለተግሳጽና ለትምህርት” የሚሆነው? ከጥንት የነበረው “ሁኒታ” አሁንም አለ ከማለት በስተቀር “ሁኒታዉን” የሚለዉጥ ምን አዲስ ነገር መጣ? መልሱን መመለስ የሚችሉት የጽሑፉ አቀባይና ተቀባይ ስለሆኑ ይህንን ለሁለቱ መምህራን እተዋለሁ። ነገር ግን ስለ ንጉሡ ዘርዕ ያዕቆብ አጭር መግለጫ መስጠት አስፈላጊ ነው።

 

ይህ ጸሐፊ በተወለደበት አካባቤ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ በነበረው አፈታሪክ መሰረት ዘርዕ ያዕቆብ የንጉሥ ዳዊት የመጨረሻ `ልጅ ነው። አፈ ታሪክ ማለት ተረት ማለት ሳይሆን በድርጊት የተደረጉ ነገሮች በቃል የሚተላለፍ ታሪክ ነው። እኛ ኢትዮጵያዉያን የሥነ ጽሑፍ ባህል ስለ አለን እንኳን የንጉሥ ታሪክ የተራ ሰዉም  በጽሑፍ ይቀመጣል። የዘርዕ ያዕቆብም ዘመነ መንግሥት ታሪክ በዓለም ታሪክ ዉስጥ ታዋቂ ቦታ ያለው ነው። ዘርዕ ያዕቆብ በጣም ገኖ የሚታወቀው “ፕሪስተር ጆን” ወይም ደግሞ “የቂስ ንጉሥ” በመባል ነው። አንድ የዉጭ አገር ታሪክ ጸሐፊ እንዳሉት “ዘርዕ ያዕቆብን የሚያህል ስመ ጥሩ ንጉሥ ከኢዛና በኋላ አልነገሰም፤ ከሱም በኋላ የመጡት ከሚኒልክ በስተቀር የሱን ያህል ሊሆኑ አልቻሉም” ይላሉ። ስለ ዘርዕ ያዕቆብ ብዙ የተጻፉ መጻሕፍት አሉ፤ ነገር ግን በሕዝብ ከአንዱ ትውልድ ወደ ሊላው ትውልድ የተላለፈው የቃል ታሪክ የሚያሳየው ምን ያህል በሕዝብ ዘንድ  ታሪካዌ ትዝታ የተወ  ታዋቂ ና ተወዳጅ መሆኑን ስለሆነ የማስታዉስውን ያህል ለአንባቢ አቀርባለሁ። በጽሑፍ ያልተደገፈ ታሪክ የሚል ከአለ አንባቢ ስለ ዘርዕ  ያዕቆብ የተጻፉ መጻሕፍትን እየፈለገ ማመሳከር ይችላል። ታሪኩ እንዲህ ነው፤ ዘርዕ ያዕቆብ የተወለደው በአዋሽ ወንዝ አካባቤ ነው፤ አፉኑም የፈታው በተወለደበት አካባቤ በሚናገሩት በኦሮሞ ቋንቋ ነበር።ገና በሕፃንነቱ እንዳለ እናቱ ንግሥት እግዚ ክብሯ የኑጉሡን ፈቃድ ጠይቃ ዘርዕ ያዕቆብን  ወደ ትውልድ አገሯ አክሱም በምትገኝው ደብረ አባይ ገዳም ለትምህርት ላከችው፤ ትግራይ በቅዱስ ቅዳሴ የታወቀ አገር ስለነበር ቅዳሴዉን አጥንቶ በአስር ዓመቱ በድቁና ማገልገሉን ይነገርለታል፤ ከዚያም ወደግሺን ማርያም በመሄድ ትርግሙና ቅኒን አጥንቷል፤ ከዚያም አልፎ አሉ በተባሉት ገዳማት እየተዘዋወረ ጾመ ድጓን አቋቋምን በሚገባ ተምሮአል። ብዙ ወንድሞች ስለነበሩት የመንገሥ እድል አገኛለሁ ብሎ አስቦ አያቅም ነበር፤ ስለዚህ እጅግ አድርጎ ያተኮረው በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ላይ ነበር፤ ለዚህም በዋቢነት ሊቀርቡ የሚችሉት ገና በወጣትነቱ ሳለ የጻፈፋቸው መጽሐፍት ናቸው፤ መጽሐፈ ሚላድ፤መጽሐፈ ብርሃን፤ መጽሐፈ ሥላሴ ናቸው። ከዚህም በላይ እጅግ ያሳስበው የነበረው የፍትሕ ጉዳይ ነበር፤ የሰው ልጅ የአለአግባብና የአለሕግ ሲጉላላ ሲያይ ሕሊናዉን በጣም ያስቸግረው ስለነበር ፍትሕ የሚያግኝበትን ዘዴ ይፈልግ ነበር፤ ከሁሉም በላይ ካህናቱ በሆነው በአልሆነው ነገር ሲታመሱ ማየቱ እጅግ በጣም ያስቸግረው ነበር፤ ስለዚህም “ሥራዓተ ቤተክርሲቲያን “ የሚል ሕግ በማውጣት ንጉሠ ነገሥት ከሆነ በኋላ ተጉለት በሚገኝው ደብረ ምጥማቅ አማኑኢል በጉባኢ ካህናቱ እንዲስማሙ አድርጓል። ይኸዉም “የሥርዓተ ኦሪት” ተከታዮችና “የሥርዓተ ወንጌል” ተከታዮች በስምምነት ተከባብረው በአንድ መቅደስ ዉስጥ አብረው እንዲቀድሱ አድርጓል። ጽላት “የሥርዓተ ኦሪት” ሕግ ስለነበር ቤተክርስቴያን ያለ ጽላት ልትቆም አትችልም፤ ይህም የሚያመለክተው ጥንታዊ ቤተመቅደሳችን የሙሴ ጽላትን ይዞ መቆየቱን ነው። ዘርዕ ያዕቅብ “ሥራዓት ቤተክርስቲያን” ያለው ዛሬ “ቀኖና” ወይም “ቀነኖ” የሚሉት ከግሪክ የመጣው ቃል “ካነን” ነው፤ ትርጉሙም ቀጥታ መስመር፤ የማያወላውል መንገድ ማለት ነው፤ ስለዚህ ትርጉሙ በማይገባቸው ቃል ከመጠቀም  ይልቅ የሊቀ ሊቃዉንቱን ዘርዕ ያዕቆብን “ሥርዓተ ቤተክርስቲያን” የሚለዉን ቢጠቀሙ የተሻለ ነበር።፡ ይህ የዘርዕ ያዕቆብ መነሻ ታሪኩ ነው።

 

ዘርዕ ያቆብ ማለት የያዕቆብ ዘር ማለት ነው፤ ነገሥታቱ የሚጠሩበት ስም ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ ነው። ለምሳሌ “ይኩኖ አምላክ” ፤ “ሥገወ ቃል”፤ “ወረደ ቃል” ፤ “ልብሰ ቃል” ፤ “ሣህለ ሥላሴ”፤ “ኅይለ መለኮት”፤  “አምኅ ሥላሴ” ፤ “በዕደ ማርያም”፤ እያሉ በክርስቴያን ስም ይጠሩ ነበር። ዘርዕ ያዕቆብ ታዋቄ መምህርም ቤሆንም ስለሰው ልጅ ያለው አስተያየት ከራሱ እምነት አብልጦ ነበር። ኦሪትንና ሐዲስን አንድ አድርጎ በመመልከት ተጣምረው እንዲሰሩ አድርጓል፤ ይኸውም የግብፁን ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ሜካኤልንና አቡነ ገበረኤልን አስማምቶ ጥንታዌት ኢትዮጵያ ጥንታዌት ጽላቷን በቤተክርስትያኗ ዉስጥ ይዛ እንድትቆይ አድርጓል፤ የምጥማቅ አማኑኢል ጉባኢ በቂ መረጃ ነው። ዘርዕ ያዕቆብ በሃይማኖት ምክንያት ምላስ አልቆረጠም፤ ካህናቱን በሽምል አልደበደም ፤ ያለምንም ደም አስተምሮ አስማማቷችዋል። ስለዚህም ነው ቄሱ ንጉሥ፤ ፈላስፋው ንጉስ የተባለበት። ዘርዕ ያዕቅብ በ35 ዓመት እድሚው ሴነግሥ ዘውዱን የጫነው አኩሱም ጽዮን ማርያም ሄዶ ነው። በዘመነ መንግሥቱ ብዙ ችግሮች ገጥመዉታል፤ “ፍትሕ” ለሕብረ ተሰቡ አስፈላጌ መሆኑን ስለተገነዘበ የራሱን ልጅ የሰው ነፍስ ስለ አጠፋ በፍርድ ሸንጎ ቀርቦ ፍርዱን እንዲያጋኝ አድርጓል፤ ምነም እንኳ ካህናቱና መኳንንቱ በልዕሉና በእናት ንግስቲት ስም ሆነው  ይቅርታ ቤጠይቁ ዘርዕ ያቆብ ከፍትሕ ጎን በመሆን ፍርድን አልገደፈም። በዚህም ምክናያት በአካባቤው የሚኖሩት ሰዎች ደብረ ብርሃን በሜግኝው መቃብሩ ላይ ፅሐይ ባለሟቋረጥ ብርሃኗን ትሰጣለች እየተባለ የሚነገርለት ስመ ጥሩ ንጉሠ ነግውሥት ነው፤ ይህም ፅሐይ በዕውነት ብርሃኗን ትሰጣለች ሳይሆን የሱን ጥሩነት ለመዘከር ታስቦ መሆኑ ግልጽ ነው። ዘርዕ ያዕቆብም ዋና ከተማውን ደብረ ብርሃን ብሎ ያለው የኮሜትን ብርሃን አይቶ እንደሆነ ይነገርለታል፤ ምናልባት ደብረ ብርሃንን የጨረቃ ከተማ የምትባለውን “ጀሪኮንን” ለማድረግ አስቦ ሊሆን ይሆናል፤ ይህም መረጃ የሊለው “ሳይሆን አይቀርም” የተባለ መላ ምት ነው፤

 

 ልዕሉ ነፍስ ስለአጠፋ በስቅላት የሞት ፍርዱን ተቀብሏል፤ እናት ነግስቲቱም ከቤተ መንግሥት ወጥታ ገዳም ገብታለች፤ ወደቤተ መንግሥቱም አልመለስም ስለ አለች ዛሪ  ያ ገዳም “እምቤ ለአፄ” እየተባለ ይጠራል። ይህ ለዘርዕ ያዕቆብ ታሪካዌ ስራው መረጃ ነው። በቄሱ ተክለ ሐዋሪያት ስም የተጠቀሰው ታሪክ መነሻው በሥረዕተ ኦሪትና ወንጌል በነበረው ያለመግባባት ነው፤ በእርግጥ ካህኑ ሥርዕት አልባ በመሆን የጉባኢዉን ዉሳኔ አልቀበልም በማለት በእስር ላይ እንዳሉ ሕይወታቸው አልፏል። ዘርዕ ያዕቆብ በሥርዕት ያምናል፤ ፍትሕ ከሰው ልጅ በላይ ሆኖ ሕግ ከአልሆነ ለሰው ልጅ የሚያመጣው መከራ ብዙ ስለሆነ መከበር አለበት በሎ ስለሚያምን ቤተሰቦቹን እንኳን ከፍትሕ በላይ አድርጎ አልተመለከታቸዉም፤ ፍርድ ሸንጎ ላይ ቀርበው ፍርዳቸዉን እንዲያገኙ አድርጓል። ይህ አልሆነም ከተባለ መረጃ አቅርቦ ዕውነተኛውን ታሪኩን መወያየት ይቻላል። የዘርዕ ያዕቆብ ተቀዳሜ ሚስቱ ንግስት እሌኒ የምትባል የሐድያ መሳፍንት ልጅ ነበረች፤ ከዘርዕ ያዕቆብም በኋላ በዋነኛነት እያማከረች የአገሩን ጸጥታና አንድነት አስጠብቃለች። የዘርዕ ያዕቆብ ታሪክ ከነቤተሰቦቹ  የሚያንጸባርቀው ጠቅላላ ኢትዮጵያን ነበር፤ ማለትም ቤተሰቡ ሙሉ የኢትዮጵያን ሕብረተሰብ ይወክል እንድነበር ይነገርልታል፤ ለዚህም ነው ታሪኩ “አረማዌ” ነው ተብሎ እንዲጻፍ የተሞከረው።

 

በቤተ መንግሥቱ ፊት ለፊት በነበረው ሜዳ ላይ፤ የመስቀል በዓል በየዓመቱ ሲከበር በሚደረገው ሥርዓት የንጉሡ ጭፍሮች በፈረስ ግልቢያ በመወዳደር እስኪ ጎዳዱና አስኪ ገዳደሉ ድረስ እርስ በራስቸው በዱላ ባጥንት በዘንግ ሲደባደቡ መንፈሳዊ አባት አዩ” በማለት ቀሴስ አስተርአየ የዘርዕ ያዕቆበን “አረማዌነት” ከወያኔ አገዛዝ ጋር እያመሳሰሉ ይጽፋሉ። ይህ ድርጊት ተደርጎም ተሰምትም ስለሚያውቅ “በፈረስ ግልቢያ” ስለ አሉት በአጭሩ ማስረዳት ለአንባቢ ይጠቅማል ብዮ አስባለሁ፤ “የፈረስ ግልቢያ” ያሉት ምናልባት በዚያ አካባቢ ሥለሚደረገው “ጉግስ” ጨዋታ ይመስላል፤ ታሪኩ እንደዚህ ነው፤ በዚያ አካባቢ ባሕል መሰረት በበዓላት ግዜ ጎልማሳዎች የሚጫወቱት “የፈረስ ጉግስ” ይባላል። በሾላ ሜዳ፤ በቡላ ሜዳ፤ በመሐል ሜዳ፤ ደበረ ብርሃን በሜገኝው በዘርዕ ያዕቅብ ሜዳ በገና፤በጥምቀት፤ታቦት በሜነግስበት ግዜ የሜጫወቱት ጨዋታ ነው። ጨዋታዉም እላይ እንደተባለው ሳይሆን ጎልማሳዎች ፈረስ ላይ ሆነው በዘንግ መከታ እየተመካከቱ ይጫወታሉ፤ ይህም ማለት በፈረስ ላይ ሆነው መከታዉን ሲጫወቱ ዘንጉ ፈረሰኝዉን መንካት የለበትም፤ በሚመካከቱም ግዜ ዘንጉ የወደቀበት ከጨዋታ ዉጭ ይሆናል፤ በስህተትም ዘንጉ ፈረሰኛውን ከነካ መችው ከጨዋታ ውጭ ይሆናል። ይህንን ጨዋታ ይህ ጸሐፊ በሕፃንነቱ ግዜ ያየው ስለሆነ ከዚህ የበለጠ መረጃ ይዞ ሊቀርብ አይችልም። ይህ ከተባለ በኋላ እነዜህ ሁለት መምሕራን ለምንድነው ዘርዕ ያዕቅብን ከወያኔ ጋር ማነፃፀር የፈለጉት? ወያኔን አሁን በሜሰራው ስራ ሊተች አይችልም? በምን አይነት ሥራአትና ደንብ የወንበዴዎችና የዘራፊዎች  ስራ ከዘርዕ ያዕቆብ ጋር ይወዳደራል? ምኒልክ ጠብቶ ያሳደገዉን የእናቱን ጡት ቆርጧል ተብሎ ጡቱን ሲቆርጥ የሚያሳይ  ሐውልት ተስርቶሎቷል፤ አንድ ስመ ጥሩ ንጉሥ በታሪካችን ዉስጥ ቤገኝ በነፍሰ ገዳይነት ተከሶ ለፍርድ ቀርቧል፤ የወያኔ ስራ ስር ነቀል ነው፤ ከዜህ በፊት ተሰራ የታባለዉን ታሪክ ማጥፋት ዋነኛ ስራው አድርጎ ስለያዘው ዘርዕ ያዕቆብን በእጅ አዙር ማጥፋት ዋና አላማው መሆኑን አንባቢ መገንዘብ ይኖርበታል፤ ወያኔ ዘርዕ ያዕቅብን የኢትዮጵያ ንጉሥ ነው ብሎ አይቀበልም፤ ኢትዮጵያ ከመቶ ዓመት በፊት ስለአልነበረች የግድ አቀባይና ተቀባይ ፈልጎ ዘርዕ ያዕቆብን ማጥፋት ግዴታ ስለሆነበት ነው “አረማዌነቱ” እንዲጻፍ የተፈለገው ። ከዜህ ሊላ ጽሑፉ የሚያሳየው ነገር የለም፤ ለዚህ  ሁሉ መልስ ስድብና ቁጣ ከሚሆን ይልቅ በተረጋጋ መንፈስ አንባቢ ተወያይቶበት ከላይ አንድ ስፍራ ላይ እንደተጠቀሰው  “መልካሙ ትውልድ “   እንዴመጣ “ሁኔታዎችን” ማመቻቸት ታሪካዌ ግዲታ ነው። ያ  መልካም ትውልድ ለመምጣት እንደ አቤል ጭኸት እየጮኽ ነው፤ “ዝመንፈስ ዘመኑ ውእቱ ዘከመዝ ቃሉ ይበጽሕ ሰማይ ወይስኪ” እንደተባለለት።  

 

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.